በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ300 በላይ ለሚሆኑ ምሁራን በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ እየተደረገላቸው ነው፡፡

ገለጻው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተደረገ ሲሆን፥ ምሁራኑ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት እና ድርጅቶች የተውጣጡ ናቸው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ ህወሓት ከለውጡ ጀምሮ የሄደበትን መንገድ እና የፈፀመውን የሃገር ክህደት ወንጀል በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል፡፡

The post በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምሁራን የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply