You are currently viewing በወቅታዊ  የአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን እስር፣ማሳደድ እና ማዋከብ አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ መግለጫ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣…

በወቅታዊ የአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን እስር፣ማሳደድ እና ማዋከብ አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ መግለጫ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣…

በወቅታዊ የአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለውን እስር፣ማሳደድ እና ማዋከብ አስመልክቶ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ መግለጫ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ተማሪዎች ማህበር(አተማ) ላለፉት አራት ዓመታት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን የማህበሩ ተቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫዎች በሆኑት የአማራ ተማሪዎች ላይ ከሚደርሰው ተደጋጋሚ ብሔር ተኮር ጥቃት እና እንደ ሕዝብ ከገጠመን ውስብስብ ችግር አኳያ እዲሁም እንደ አንድ የቁርጥ ቀን የአማራ ተቋም የራሱን ሚና ሲወጣ የቆየ መሆኑ እውቅ ነው ። ነገር ግን ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ተቋማዊ ስራዎችን ሲያከናውን ሁኔታዎቹ ሁሉ አልጋ ባልጋ ሁነውለት ሳይሆን ይልቁኑ ከተመሰረተበት ዋነኛ አላማ አንፃር የአማራ ተማሪዎችን መብት ለማስከበር ከተመሰረተበት እለት ጀምሮ እስከአሁኗ ሰአት ድርስ በበዙ ፈተናዎች መካከል አንዴ ሲወድቅ አንዴ ሲነሳ የአገዛዙን በትር ተቋቁሞ ተቋማዊ ህልውናውን እያስቀጠለ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በመሆኑም እነዚህ ፈተናዎች በተቋማችን ላይ እንዲሁም የአማራ ህዝብ ላይ የቀጠሉ ሲሆን ለዘመናት አማራ ላይ የተሰሩ የጥላቻ ትርክቶች ከእለት እለት እያደጉ፣ከጊዜ ጊዜ እየሰፉ መጠው አሁን ባለበት ደረጃ ደርሰዋል። ይኸውም ህዝባዊ እና ስርአት አቀፍ በመሆን አማራው ላይ የጥፋት የአዋጅ ነጋሪት ድለቃ በሁሉም አማራ ባለበት የኢትዮጵያ ክፍል ሀገራት በሞላ ተባብሶ ቀጥሏል።በዚህም የአማራ ተቋማት አመራር እና ሙህራን የሆኑ ሁሉ የኦነጋዊዉ የጥፋት ዘመቻ ግንባር ቀደም ሰለባ ሆነው ይገኛሉ። በመሆኑም እኒህ የአማራ ተቋማት አመራሮች እና ሙህራን በያሉበት ሽብርተኛ የሚል የተለመደ የድራማ ክስ እየተለጠፈባቸው እየተሳደዱ ፣እየታሰሩ እና እየተገላቱ ይገኛል።በዚህም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የቀድሞ እና አዲስ አመራሮች እየተሳደዱ ፣እየታሰሩ እና እየተንገላቱ ይገኛሉ። ከነዚህም መካከል 1) የቀድሞው የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራር የነበረው ሀብተ ማሪያም ሞላ በትንሳየ ዋዜማ ማለትም ሚያዚያ 08/08/15 ዓ.ም እለታዊ ስራውን እያከናወነ ባለበት በፀጥታ አካላት ታፍኖ ወደ ባህርዳር አንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደ በኃላ ለቀናት ያለፍርድ በዚያው ቆይቶ ነገር ግን ከብዙ የፍትህ ይሰጠኝ ልፋት እና ውትወታ በኃላ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ችሏል ሆኖም በአገዛዙ የተጓተተ የፍትህ አሰጣጥ ስርአት ምክኒያት መግለጫውን እስካወጣንበት ሰአት ድረስ በባህርዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በግፍ ታስሮ ይገኛል። 2) የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ም/ፕሬዚዳንት ሲሳይ መልካሙ በሽብር ወንጀል ተጠርጥርሀል በሚል ሚያዝያ 21/2015 ዓ.ም ምሽት አካባቢ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ሸዋ ዳቦ አካባቢ በደህነት እና በፖሊስ አባላት ታፍኖ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዶ ያደረ ቢሆንም በቀጣዩ ቀን ማለትም ሚያዚያ 22/2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት አካባቢ በአውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ሜክሲኮ ማረሚያ ቤት ተወስዶ በስውር ታስሮ ለቀናት ከቆየ በኃላ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሚያዝያ 24/2015 ዓ.ም ከሌሎች በግፍ ከታሰሩ የአማራ ታጋዮች ጋር ቀርቦ ፖሊስ ለምርመራ በሚል የጠየቀውን 14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶበት ግንቦት 9/2015 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጦባቸዋል። በመሆኑም አሁን ላይ ከሜክሲኮ እስር ቤት ወጠው ወደ ማዕከላዊ ተዘዋውረዋል። ሲሳይ መልካሙ የሁለተኛ ድግሪ ማስተርስ ተማሪ ሁኖ ሳለ የአማራ ተወላጅ እና የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራር በመሆኑ ብቻ ሽብርተኛ ነህ የሚል የተለመደ የክስ ታርጋ ተለጥፎበት በግፍ ታስሮ ይገኛል። 3) የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የአደረጃጀት ጉዳይ ሀላፊ የሆነው እዲሁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 3ኛ አመት የህግ ተማሪ የሆነው ዮሐንስ ተሻገር ትምህርቱን በመማር ላይ ባለበት ሚያዚያ 10/15 ዓ.ም ታፍኖ ሜክሲኮ ማረሚያ ቤት ተወስዶ ለቀናት በተለያየ ፍርድ ውጣ ውረድ አልፎ የዋስትና መብቱ ሚያዚያ 30/15 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጠብቆለት የዋስትና 6ሺ ብር ከተከፈለ በኃላ ከእስር መለቀቁን ስንጠብቅ ህግ የማይገዛው ወንበዴው ስርአት እደገና በሽብር ወንጀል ትፈለጋለህ በሚል በእስር ካቆየው በኃላ በቀን 02/09/15 ዓ.ም በሽብር ወንጀል ፍርድቤት ቀርቦ የ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጦበት ለግንቦት 16/15 ዓ.ም ተቀጥሯል። 4) ተማሪ እዘዝ ሞላ ተሻለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ አመት የህዝብ አስተዳደሪ ልማት ተማሪ ሲሆን እዲሁም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስፈፃሚ አባል መሆኑ ይታወቃል ሆኖም እዘዝ ሞላ በቀን 03/09/15 ዓ.ም ከቤተክርስቲያን ሲመለስ ማንነታቸው ባልታወቁ ሲቪል ለባሾች ከምሽቱ 12:15 ታፍኖ የት እደተወሰደ አልታወቀም። አፋኙ ስርአት ተማሪ እዘዝ ሞላን መግለጫው እስከተፃፈበት ሰዓት ድረስ የት እዳደረሰው የታወቀ ነገር የለም። በዚህ ሁሉ ሳያበቃ ይህ ኦነግ መራሽ ፀረ-አማራ ስርዓት ግንቦት 09/09/15 ዓ.ም ዋና መቀመጫውን ባህርዳር ያረገውን የማህበራችን ቢሮ እንደ ወንበዴ ሰብሮ በመግባት ዘረፋ ፈፅሟል። በመሆኑም የተለያዩ የሰነዶች መዛባት ፣መሰረዝ እዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን ጨምሮ ቢጠፉ እና ቢወድሙ አገዛዙ ሀላፊነቱን እደሚወስድ ለማሳወቅ እንወዳለን። በጨረሻም አፋኙ ስርአት አማራ ላይ እና የአማራ የሆነው ነገር ሁሉ ላይ የሚያደርሰውን የጥፋት እርምጃ በአስቸኳይ አቁሞ የቀድሞው እና የአሁን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራሮች እና አባላት ላይ፣ሌሎች የአማራ ተቋማት አመራር እና አባላት ላይ ፣ በየደረጃው ያሉ የአማራ ፋኖ አባላት ላይ ፣ የአማራ ሊህቃን ላይ እንዲሁም ሁሉም የአማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን እስር፣ማሳደድ እና ማዋከብ እዲያቆም እንዲሁም የታሰሩትን በአስቸኳይ እዲፈታ ስንል በማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ስም እጠይቃለን። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply