
#በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የወጣ መግለጫ:- ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በትናትናው እለት ማለትም በቀን 06/11/15 ዓ.ም ራያ ቆቦ ከተማን ጨምሮ አራዱም ፣አሳመምቻ ፣ቀመሌ ተክለሃይማኖት ፣ጠዘጠዛ ፣ሮቢት እና ጎብዬ ዙርያ ባሉ አካባቢዎች በዋርካው ምሬ ወዳጆ በሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ላይ በአገዛዙ የኦሮሙማ ስርአት የተከፈተው ጦርነት ባለፉት ሀያ ሰባት አመታታ በልዩነት አማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈፅም የነበረውን የወያኔን ስርአት ፍላጎት ለማስፈፀም የሚደረግ የጦር ወንጀል ነው። ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ባደረገው ማጣራት የገዥው ሰርዐት በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም በፖርላማ በሽብር ብድን የተፈረጀውን እና ትናት በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ቦታዎች ላይ ለምሳሌ በወለጋ ፣ በጉትን፣ በሆሩ ጉድሩ፣ ወዘተ ላይ በሚኖሩ አማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመውን የኦነግ ሰራዊት ወደ አማራ ክልል እያስገባ መሆኑን ደርሰንበታል ። በሆኑም ትናት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ላይ የዘመተው ሰራዎት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦነግ ሰራዊት ጥምር ጦር እደሆነ ደርሰንበታል። ባለፉት ወራት ውስጥ ህግ ለማስከበር በማለት አማራ ክልል ላይ በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተው ጦርነት ከጅምሩ አሸባሪ ቡድንን ህግ አስከባሪ አርጎ ማስገባት የስርዐቱን የለየለት ጨፍጫፊነት የሚያሳይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በመላው ሀገሪቱ የሚጨፈጨፉ አማሮችን የደህንነት ከለላ ሳይሰጥ በአማራ ክልል ምንም የሰላም ችግር በሌለበት ሁኔታ ጦር ማዝመት የስርዐቱን አማራውን ሁለንተናዊ እረፍት ነስቶ በአፋጣኝ ህልውናውን ለመንጠቅ የሚደረግ ዘመቻ መሆኑን ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ለመላው የአማራ ህዝብ ለማስገንዘብ እንወዳለን። በመጨረሻም ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር ( አተማ ) የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል 1) መንግስት ህግ ለማስከበር በሚል አማራ ክልል ላይ እየፈፀመው ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአፋጣይ እዲያቆም ጥሪ እናስተላልፋለን፣ 2) መንግስት በኢትዮጲያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም ወደ አማራ ክልል ያስገባውን የኦነግ ሰራዊት በአፋጣኝ እዲያስወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን፣ 3) መንግስት ፋኖነት የአማራ አንዱ ባህላዊ ስርዐት ወይም መገለጫ መሆኑን ተገንዝቦ አሁን እያደረገው ያለውን ይህንን የአማራ ባህል የማጥፋት ወንጀል እዲያቆም ጥሪ እናደርጋለን፣ 4) መላው የአማራ ህዝብ የተከፈተበት ጦርነት ህልውናውን እስከ ወዲያኛው ለመንጠቅ የሚደረግ ጭፍጨፋ መሆኑን በልኩ ተገንዝቦ ህልውናውን በአንድነት በመቆም እዲያስጠብቅ ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post