You are currently viewing በወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ “የእሳት ቅብብሎሽ!!! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣    የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከተከበረ፣ከ…

በወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ “የእሳት ቅብብሎሽ!!! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከተከበረ፣ከ…

በወቅታዊ ጉዳዮች ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ “የእሳት ቅብብሎሽ!!! የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከተከበረ፣ከታፈረና ኃያል ልዕልናው ተወርውሮ ወርዶ በመሠረተው ሀገረ መንግሥት ውስጥ በዓለም ላይ ተፈጽሞ የማያውቅ ግፍና በደል እያስተናገደ ይገኛል።ግፉ የሚመነጭበትን ሥርዓትና መከራውን የሚያስፈጽሙ የሥርዓቱን ታዳሚዎች ተቃውሞ መከራውን የሚገታ፣የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነቱን የሚያረጋግጥ በወርድና ቁመቱ ልክ የሆነ ተቋማትን ሲመሠርት ደግሞ ሥርዓቱ የበለጠ ጥርስ አውጥቶ ተቋማቱን እየናደ የተቋሙ መሪዎቹን እያንገላታ ቆይቷል። ሥርዓቱ ከራሱ ርእዮተ ዓለምና ስትራቴጅካዊ(ስልታዊ) እቅድ ውጭ ሆነው የሚወለዱ የአማራ ተቋማትን በራሳቸው ቁመው የሚሞሉትን ጎዶሎ በመረዳት የሚያቀራርቡ ማዕከላዊ ሐሣቦችን ከማምጣና መንግሥታዊ ድርሻውን ከመተግበር ይልቅ በማፍረስ አመራርና አባላቱን በማሰርና በማፈናቀል ራሱን ብቸኛ መዳኛ አደርጎ ሲያቀርብ ኖሯል።የአማራ ተማሪዎች ማህበርም የራሱን መልክና መቋሚያ ሐሳብ ይዞ ከተወለደበት 2010 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ተቋሙ፣ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚና አባላቱ በሥርዓቱ ጥርስ ውስጥ ገብተው ቆይተዋል። በዚህም ወላጆቻችን ባድማቸውን ቆርሰው በመስጠት የመሠረቷቸውና ማህበረሰብ ዓቀፍ ተጠቃሚ መሆን ከነበረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ሳይቀር እየተንገላቱና ከትምህርት ገበታ እየተባረሩ ይገኛሉ። የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ በበዙ ፈተናዎች እና ጥልፍልፎሽ መካከል እያለፈ የመጣ ተቋም ከመሆኑ አንጻር እነዚህን ፈተናዎች በበሳል እና ቁርጠኛ ልጆቹ ጥበብ የተሞላበት አመራር እና ትግል አማካኝነት እያለፋቸው የመጣ መሆኑ እውቅ ነው። በቀን 28/05/2015 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ አዲስ ስራ አስፈጻሚዎችም ተቋሙ ሲወለድ ይዟቸው የተወለደውን ዓላማዎች ለማሳካት ከመትጋትና በተቋማዊ ስትራቴጅክ እቅዱ ከመመራት ይልቅ ሥርዓት ወለድ ወቅታዊ ችግሮችን መፍታት ላይ ተጠምደዋል።ይህም የአተማን የአመራር ሽግግር የእሳት ቅብብሎሽ አድርጎታል። ዛሬም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አዲሱ ስራ አስፈጻሚ በተመረጠ ማግስት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የአማራ ተማሪዎች ላይ ብሔርን ትኩረት ያደረገ ጥቃት ማለትም ዝርፊያ፣ከትምህርት ገበታ መባረር፣ድብደባ እዲሁም የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶች እና የመብት መገፈፎች እየደረሰባቸው መሆኑን ከመስማታችን በተጨማሪ የነቁ እና የበቁ የቀድሞው የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችን የአማራ ታጋዮችን ማሰር፣ማሳደድ እና ማዋከብ የቀጠለ መሆኑን ስናይ ተቋማችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) እንደ አንድ የአማራ ተቋም ከፈተና ወደ ሌላ ከፍ ያለ ፈተና ሽግርግሮሽ ውስጥ መሆኑን ወይም የእሳት ቅብብሎሽ ሒደት ላይ እንደሆነ ተረድተናል። በመሆኑም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በወቅታዊ ጉዳዮች ማለትም በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ፣በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፣በጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፣በደቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ያሉ የአማራ ተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ባለው ብሔር ተኮር ጥቃት እንዲሁም የቀድሞው የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራሮችን ጨምሮ በበቁ እና በነቁ የአማራ ታጋዮች ላይ የሚደረገውን እስር፣ ማሳደድ እና ማዋከብ በመቃወም የሚከተለውን ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡- 1) በመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ አርበኛ ዘመነ ካሴን እና የታሪክ ምሁሩን አቶ ታዲዮስ ታንቱን ጨምሮ በሀገሪቱ በግፍ የታሰሩ ፋኖዎች እና ሌሎች ታጋዮች ፍትሕ እዲሰጣቸው በሰላማዊ መንገድ ድምጽ ባሰሙበት ሰልፍ ላይ ሰልፉን አስተባብራችኃል እንዲሁም መርታችኃል ያሏቸውን ሰባት የአማራ ተማሪዎች ማለትም ~ አበበ ወንድም ….. ……የሁለተኛ አመት “Narm” ተማሪ ~ መልካሙ አይናዲስ …..የአንደኛ አመት “freshman course” ተማሪ ~ ውለታው ፈጠነ…………የአንደኛ አመት “freshman course” ተማሪ ~ ግርማ አድማሴ………. የአንደኛ አመት “freshman course” ተማሪ ~ ሰሎሞን አለበል ………..ሁለተኛ አመት “physics” ተማሪ ~ ካሳ እያዩ ……………… አራተኛ አመት “physics” ተማሪ ~ ሀብታሙ አበባው…….. ሁለተኛ አመት “computer science” ተማሪ ከትምህርት ገበታቸው አባሯል። በመሆኑም ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ዩኒቨርሲቲዉ ጉዳዩን እንደገና አጢኖ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ከበታቸው እዲመልሳቸው ያሳስባል። 2) የአማራ ተማሪዎችን በማሳገት የሚታወቀው የደቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የ17ጡ የታገቱ ሴት የአማራ ተማሪዎች ጉዳይ መቋጫ ሳያገኝ በድጋሚ ስምንት የአማራ ተማሪዎች በደቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ በመማር ላይ ባሉበት ታግተዋል ።በመሆኑም የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) እነዚህን የአማራ ተማሪዎች የሚመለከተው አካል ሁሉ ተነጋግሮ ከታገቱበት እዲለቀቁ እዲያደርግ እንዲሁም አጋቹን ሃይል ለሕግ እዲያቀርብ ያሳስባል። 3) በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የአማራ ተማሪዎች ላይ የሚደረገው ብሔርን ትኩረት ያደረገ ዘረፋ ፣ድብደባ እና ማዋከብ እንዲቆም ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የሚመለከታቸውን ዩኒቨርሲቲዎች እና የመንግሥት አካላትን ያሳስባል። 4) ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የቀድሞ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) አመራሮችን ጨምሮ የነቁ እና የበቁ የአማራ ታጋዮች ላይ የሚደረገውን እስር፣ማሳደድ እና ማዋከብ እንዲቆም የሚመለከተውን ሁሉ ያሳስባል። በመጨረሻም ማሀበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ከላይ የጠየቅናቸው ጥያቄዎች የማይመለሱ ከሆነ አባላቱን፣ደጋፊውን እዲሁም ከጥግ እስከ ጥግ ያለውን የአማራ ተማሪ አስተባብሮ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ወደሚመልስና ሕዝባዊ የመከራ ቀንበሩን ወደሚያሽቀነጥር ከፍ ያለ የትግል እንቅስቃሴ የምንገባ መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን። አተማ፡የአማራ ትውልድ ተቋም!! የካቲት ፳፩/፳፻፲፭ ዓ.ም “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply