በወባ ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡የጤና ሚንስቴር በመላው አፍሪካ የወባ ትንኝ ቀጥጥር ማህበር (Pan-Afri…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/NgTS5FJMdFY56wSbkCLNYSzHiS9CvVKtXxG5LS76szVO4XP02HjY4HTAwQZSGRS7s8IdRV3YC7ekZelSDKJmdaAYvJ6mgWk5u3WOpuuOhjf0G3v63ImaAZW-TgKMQoaV1lGJyW5dpHbIzGvNv9OPNx9-Y0srQ-YJNCMToHmYg5PHMd5S_EuuCH_AIPHVaVw-t126c4f55u6tpLJM4SRiHAoKkg7B5QK7IBxkRsTu0w5f0UudtliPejgR7lfNcOrsGPtk0U5o8K_80YRrgRIzaFQu2sU4HXPFwZTmFsznk-BimW22KbC07KVJKU4Ay_G81VUkOmijZvuCJNfHm0kzDQ.jpg

በወባ ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊካሄድ ነው፡፡

የጤና ሚንስቴር በመላው አፍሪካ የወባ ትንኝ ቀጥጥር ማህበር (Pan-African Mosquito Control Association) ጋር በመተባበር፣9ኛውን በወባ ወረርሽኝ ዙሪያ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የሚካሄደው ዓመታዊ ኮንፈረንስ ከመስከረም 7 – 11 ቀን 2016 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጧል።

በኮንፈረንሱ ላይ ከአፍሪካ እና ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ከ850 እስከ 1000 የሚጠጉ ከጤና ጋር የተገናኙ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣ ኢንዱስትሪዎች እና የግል ዘርፎች ይገኙበታል ተብሏል።

9ኛው በወባ ወረርሽኝ ዙሪያ ላይ ያተኮረ ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና ኤግዚቢሽን በኢትዮጵያ መካሄዱ አዳዲስ የምርምር ግኝቶችን ለማስተዋወቅና በትብብር ለመስራት እድሎችን በማመቻቸት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተመላክቷል።

በእሌኒ ግዛቸው

መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply