
በወንድማችን አሸናፊ አካሉ ላይ የባሕር ዳር አድማ ብተና ፖሊሶች የፈጸሙትን አስገድዶ ስወራ ወንጀል አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የባሕር ዳር ጽ/ቤት የፃፈውን ደብዳቤ አያይዘናል ሲሉ የአብን ስራ አስፈፃሚ እና የፓርላማ አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ አስታወቁ! ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፀጥታ መዋቅር የዜጎችን ደኅነንት መጠበቅ ቢያቅተው እንኳን በንፁኃን ዜጎች እገታ ላይ በዚህ መልኩ የሚፈጽመው ወንጀል አሳፋሪ ነው። ወንድማችን አሸናፊ አካሉን ከእገታ ይለቅ ዘንድ ዛሬም የይልቃል ከፋለን መንግስት በአጽንዖት እንጠይቃለን ብለዋል አቶ ክርስቲያን ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post