በወንድሞችህና በንፁሃን ደም መታጠብህን አቁምህ ከአርቆ አሳቢው ህዝብህ ጎን እንድትቆም በጥብቅ እናሳውቃለን ብለዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! አንተ ሰላም እንድታድር ጐረቤትህ ሰላም ይደር እንደተባለው አማራ እስከዛሬ ብቻውን ታርዶ፣ ተጨፍጭፎ ፣ በር ተዘግቶ መላ ቤተሰቡ በእሣት ሲጋይ፤ የሰውነት ክብሩን ተነጥቆ ለአፈር ሳይበቃ የትም ሲጣል፣ የቤቴ በር ካልተንኳኳ ብለህ ዝም ያልኸው የአገራችን ህዝብ ሆይ ዛሬ አማራ የመጨረሻው የህልውና ትግል ውስጥ ገብቷልና አገራችን ወደማይሆን አቅጣጫ ከመሄዷ በፊት በህዝባዊ ሰላማዊ ትግል የህልውና ትግሉን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ የተረኛ መንግሥት አገር የመምራት እና የማስተዳደር ብቃት ስለሌለው፤ ህዝብ አገሩን ለማዳን የሚያምንባቸው አቅምና ብቃት ያላቸውን ሰዎች አሰባስቦ የሽግግር መንግሥት ለመመስረት እንዲዘጋጅ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። አማራ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ይጎናፀፋል! ድል ለአማራ ህዝብ!
Source: Link to the Post