በወዳጅነት ጨዋታ ዋልያዎቹ በዛምቢያ አቻቸው ተረቱ

በወዳጅነት ጨዋታ ዋልያዎቹ በዛምቢያ አቻቸው ተረቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከዛምቢያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አካሂደዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ እስከ 86ኛው ደቂቃ ድረስ 2-1 ስትመራ ብትቆይም፤ ተቀይሮ የገባው አልበርት ካዋንዳ አከታትሎ ባስቆጠራቸው ጎሎች የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን 2ለ3 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አሸንፎ ወጥቷል።

የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን የማሸነፊያ ጎሎችን ሙጋምባ ካምፖምባ በ39ኛው ደቂቃ፣ እንዲሁም አልበርት ካዋንዳ በ86ኛው እና በ90ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለት ጎሎች ግሞ ጌታነህ ከበደ በ13ኛው ደቂቃ እንዲሁም አስቻለው ታመነ በ43ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል።

The post በወዳጅነት ጨዋታ ዋልያዎቹ በዛምቢያ አቻቸው ተረቱ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply