በዋርካው ምሬው ወዳጆ የሚመራው ምስራቅ አማራ ፋኖ ማን ነው? ምስራቅ አማራ ፋኖ የህልዉና አደጋ የተጋረጠበትን የአማራ ህዝብ ትግል የያዘ የፋኖ አደረጃጀት ነው። ከስያሜው ስንነሳ ወሎን…

በዋርካው ምሬው ወዳጆ የሚመራው ምስራቅ አማራ ፋኖ ማን ነው? ምስራቅ አማራ ፋኖ የህልዉና አደጋ የተጋረጠበትን የአማራ ህዝብ ትግል የያዘ የፋኖ አደረጃጀት ነው። ከስያሜው ስንነሳ ወሎን እና አዲስ አበባን ጨምሮ ሸዋን የያዘ ሲሆን ምዕራብ አማራዉን ጎጃምና ጎንደርን ጨምሮ በአጠቃላይ በአንድ ዕዝ የሚመራ አንድ የአማራ ፋኖ ለመመስረትም ቅርብ አደረጃጀት ነው። መነሻው የራያ ፋኖ ሲሆን ከዛም በትግል ሂደት ሙሉ ወሎን እያሰባሰበ ደሴ ላይ ወደ ወሎ ፋኖ አድጎ ከሸዋ ፋኖዎች ጋር በጥምረት መስራት ሲጀምር ስያሜው አሁን ላይ ወደሚጠራበት ምስራቅ አማራ ፋኖ ተቀይሯል። በቀጣይም ወደ አንድ አማራ ፋኖ ለማምጣት በሚደረገው የምስረታ ሂደት ዉስጥ ጉልህ ሚና በመጫወት የአምበሳዉን ድርሻ እንደሚወጣ ይጠበቃል። በትግል ሂደትም ከራያ ጀምሮ አላዉሃ ሸነቲ ተራራ በወልድያ ተራራማ አካባቢዎች በድሬ ሮቃ በሃይቅ ቢስጢማና ቦኮክሳ እንዲሁም ሚሌ ኮቲቻ በደሴ ቦሩ ስላሴ እና ጦሳ ተራራ በመካነሰላም ግንባር በቀይ መብራት በወግዲ በልጓማ በገነቴ በፊንጭፍቱ በኢላዳ በአቀስታ ዶባ እና መርከብ ተራራ እስከ ቱሉ አውሊያ እና አሁን ምሽግ እስከሚገኝበት ራያ ግንባር ድረስ በርካታ አውደ ዉጊያዎችን ያደረገ እና አገሩን ኢትዮጵያን ከመፍረስ የታደገ ባለ ትልቅ ታሪክና የአባቶቹ ልጅ የሆነ ፋኖነትን በተግባር ያሳየ ተቋም ነው። አሁን ላይ ከ80 በላይ መስዋዕትነት የከፈሉ እና ከ130 በላይ ቁስለኞች በእጁ ይዞ ራያ ግንባር ላይ ከጠላት ጋር ምሽግ ላይ ተፋጦ የሚገኝ ተቋም ነው። በመሆኑም ይህንን የአማራን ህዝብ ከተጋረጠበት የህልዉና አደጋ ለመታደግ ቆርጦ የተነሳ ፋኖ ለመበተንና ለማዳከም (ባይቻልም) ከራሱ ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጋር የነበሩ ሌብነትን ጨምሮ በግድያ ፋኖን ለማፍረስ ከጠላት ተልዕኮ ተቀብለው የሚሰሩ እና በተለያዩ ከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለቶች የተሰናበቱ የቀድሞ አባሎቹ ሌሎች አላማቸዉን በቅጡ ያልተረዱ አካላትን ጨምረው የወሎ መዲና በሆነችው ደሴ ከተማ የወሎ ፋኖ መሰረትን በሚል ህዝባችንን በማህበራዊ ሚዲያ እያደናገሩት ይገኛሉ። ስለሆነም ምስራቅ አማራ ፋኖ ማለት በዋናነት የወሎ ፋኖን ያቀፈ የፋኖ ተቋም ሆኖ እያለ ምስራቅ አማራ ፋኖ ብለው የሰየሙት ወሎ ማለት ስለማይፈልጉ ነው በሚል ህዝብ እያደናገሩና የአማራን ህዝብ ትግል እያዳከሙ መሆኑን መላው የአማራ ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን። በመጨረሻም ዛሬም እንደ ትናንቱ አማራ ተቋም ሲመሰርት ተቋሙን ሊያፈርሱበት የሚንቀሳቀሱ ሆዳም አማራዎችን በትግስትና በዝምታ የምናይበትና የምናልፍበት ምዕራፍ ሊያከትም ይገባል መልክታችን ነው። ” ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው።”

Source: Link to the Post

Leave a Reply