በዋስ እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ወንጌላዊ ቢኒያም ከእስር አልተፈቱም

https://gdb.voanews.com/851896DB-628D-4879-9EE9-81D1D64F1935_w800_h450.jpg

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ፓስተር ቢኒያም ሽታዬ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት መሄዱን ጠበቃቸው ገለጹ።

ጥር 14/2015 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተፈጥሮ ከነበረው ችግር ጋራ በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የካቲት 3/2015 ዓ.ም የተያዙት ወንጌላዊ ቢኒያም ሽታዬ፣ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ወንጀል ጠርጥሪያቸዋለሁ በሚል ፍርድ ቤት አቅርቧቸው ጉዳያቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከ33 ጠበቆቻቸው መካከል አንዱ ጠበቃና የህግ አማካሪ ብሩክ ደረጀ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡፡

የካቲት 17 ቀን ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የ5,000 ብር ዋስትና አስይዘው እንዲወጡ ቢፈቀድም ፖሊስ ይግባኝ በማቅረብ በእስር ላይ እንዳቆያቸውም የገለጹት ጠበቃው፣ ጉዳያቸው አሁን ወደ አዲስ አበባ ፍርድ ቤት ወርዶ እየታየ መሆኑንም አብራርተዋል፡

በተለያዩ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዋስትና ቢፈቀድላቸውም፣ ፖሊስ በፌዴራል ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች ያለውን ይግባኝ ካጠናቀቀ በኋላ፣ ዛሬ ጉዳዩን ወደ አዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ምድብ ችሎት ወስዶት እዚያም ዋስትና ተፈቅዶላቸው ፖሊስ ይግባኝ ማቅረቡን ከጠበቆቻቸው አንዱ ጠበቃ ብሩክ ደረጀ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply