You are currently viewing በዋሽንግተን የተለያዩ ማህበራት በጋራ በመሆን ለጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ልዩ የውይይት እና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር አከናውነዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

በዋሽንግተን የተለያዩ ማህበራት በጋራ በመሆን ለጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ልዩ የውይይት እና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር አከናውነዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ም…

በዋሽንግተን የተለያዩ ማህበራት በጋራ በመሆን ለጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ልዩ የውይይት እና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር አከናውነዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በታላቁ የአማራ ኮንቬንሽን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ፌዴሬሽን (ፋና) እና የካናዳ የአማራ ማህበራት ህብረት (ካሳ) አዘጋጅነት እንዲሁም በዋሽንግተን አካባቢ የአማራ ማህበር ስፖንሰር አድራጊነት ለጋዜጠኛ፣ መምህርት እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች መዓዛ መሀመድ ልዩ የውይይት እና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ማከናወናቸውን አስታውቀዋል። በታላቁ የአማራ ስብሰባ በዋሽንግተን ዲሲ ስለ አማራ ሕዝብ የወደፊት ጉዞ ሰፊ ምክክር ስለመደረጉም ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አጋርተዋል። የዚህ ዝግጅት ስፖንሰር ከተመሠረተ ሶስት ወር ያልደፈነው የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የአማራ ማሕበር (Washington Area Amhara Association – WAAA) ሲሆን፤ አዘጋጆች የሰሜን አሜሪካ የአማራ ማሕበራት ፌደሬሽን ወይም ፋና (Federation of Amhara Associations in North America – FANA) እና በካናዳ የአማራ ማሕበራት ስብስብ – ካሳ ለዐማራ (Canadian Amhara Societies Alliance – CASA AMHARA) ናቸው። “ትግላችን እስከ ነጻነት ይቀጥላል!” ያሉት ዶ/ር ደሳለኝ ውጤታማ ሲሉ የጠሩትን ስብሰባ ላዘጋጁ፣ ለተሳተፉ ወገኖች በሙሉ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply