በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚገኙ ሕፃናት የዓድዋ በዓል አከባበር

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-dfc8-08db1f455c0e_tv_w800_h450.jpg

ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የሚገኙ ህፃናት 127ኛ ዓመት የዓድዋ ድል በዓልን ቅዳሜ ምሽት ቨርጂኒያ ውስጥ በተከናወነ ልዩ ዝግጅት አክብረዋል።

ከኢትዮጵያ ውጪ የተወለዱና በልጅነታቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመጡ ህፃናትና አዳጊዎች የመጡበትን ቋንቋ፣ ባህል፣ ልማድ እና መከባበር አውቀው እንዲያድጉ ለማገዝ የተቋቋመ አቡጊዳ የቋንቋና የባሕል ተቋም የመርኃ ግብሩ አሰናጅ ነበር።

ከአራት ዓመት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ግዛት የተቋቋመው ይህ ተቋም ከመደበኛ የትምህርት መርሐ ግብሮቹ ጎን ለጎን ህጻናትና ታዳጊዎች የሚሳተፉበት ኪናዊ መድረኮችንም ያሰናዳል።

የአድዋን ድል በዓል በማስመልከት ቅዳሜ የካቲት 25/2015 ዓ.ም በህፃናቱ የቀረበውን ልዩ ዝግጅት በተመለከተ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply