በዋሽንግተን ዲሲ የህሊና እስረኞች እነ እስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባ…

በዋሽንግተን ዲሲ የህሊና እስረኞች እነ እስክንድር ነጋ እንዲፈቱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የእነ እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌን እስር በመቃወም በዋሽንግተን ዲስ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደው። ከፍተኛ ቅዝቃዜ እና የበረዶ ዶፍ ዝናብ ሰለማዊ ሰልፍ በታቀደው መልኩ ለማካሄድ አስቸጋሪ ቢያደርገውም ሰልፈኞቹ የበረዶ ዶፉን በመቋቋም ንጹሃን የህሊና እስረኞች ፍትሕ እንዲያገኙ ጠይቋል ብሏል ባልደራስ። የባልደራስ እና የባልደራስ መኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ለውጥ እንዲመጣ በሚል ባደረጉት ትግል ለበርካታ ዓመታት በሕወሓት መራሹ ስርዓት በቃሊቲ በግ ተሰቃይተው በህዝብ ተጋድሎ የተፈቱ ናቸው። ይሁን እንጅ የህዝብ ትግልን ወደራሱ በመውሰድ የለውጥ ኃይል ነኝ የሚለው ቡድን ከመጣ ባለፉት 2 ዓመት ተኩል በላይ እየሄደበት ያለው መንገድ የተረኝነት እንጅ መሰረታዊ ለውጥ የሚያመጣ አይደለም እያሉ የዘር ማጥፋቱን፣ግድያውን፣የመሬት ወረራውንና መፈናቀሉ በብርቱ ሲቃወሙና ሲያጋልጡ ነበር። ከህጻናት ልጆቿ ነጥሎ ያሰራት አስቴር ስዩምን ጨምሮ፣ስንታየሁ ቸኮልና አስካለ ደምሌ በተለያየ ጊዜ ሲፈፀምባቸው የነበረው እስርና እንግልት ሳይበግራቸው የለውጥ ኃይል ነኝ ያለውን ስርዓት ብልሹ አካሄድ በባልደራስ ውስጥ ሆነው እየታገሉ ሳለ ነው የአርቲስት ሀጫሉን ግድያን ተከትሎ በፈጠራ ክስ የታሰሩት ሲል ባልደራስ በተደጋጋሚ ይገልጣል። እስክንድር ነጋ ገና ባልደራስን ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ጦርነት እንገባለን ማለታቸው አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply