በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች በተደራጁ ጽንፈኞች ጥቃት ተፈጽሞብናል አሉ፤ ይህን ተከትሎም ከግቢ በመውጣት በቤተ ክርስቲያን ግቢ ለመጠልል ተገደናል ሲሉ ተናግረዋል። አማራ ሚዲ…

በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች በተደራጁ ጽንፈኞች ጥቃት ተፈጽሞብናል አሉ፤ ይህን ተከትሎም ከግቢ በመውጣት በቤተ ክርስቲያን ግቢ ለመጠልል ተገደናል ሲሉ ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደቡብ ኢትዮጵያ ዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የአማራ ተማሪዎች ሰንደቅ አላማንና የአጼዎች ምስል ያለበትን ቲሸርት የቀደዱ ጽንፈኞች ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ገልጸዋል። የተፈጸመውን የተደረጀ ጥቃት ተከትሎም ከግቢ ለመውጣትና በዋቻሞ ኪዳነ ምህረት ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግረዋል። የካቲት 23/2014 በዋቻሞ ዩኒቨርስቲ በዓል ከቤተ ክርስቲያን የነበሩ ተማሪዎች አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ አላማ ይዘው፣ የቀደምት ጀግኖች ምስል ያለበትን ቲሸርት ለብሰው የዓድዋ ድል በዓል በሚያከብሩበት ወቅት ቀድመው በአዳራሽ በመሰብሰብ በዓሉ እንዳይከበር ረብሻ በማስነሳት ድብቅ የኦነግን አላማ ለማስፈጸም የተዘጋጁት የኦሮሞ ተማሪዎች ባንዴራ በመቀማት ቀደው በመጣል ትንኩሳ ማድረጋቸው ተገልጧል። ቤተ ክርስቲያን ቆይተው የሚመጡ ሴት ተማሪዎችን ነጠላ ሲቀሙ እና በኮብል ስቶን ሲደበድቡም ተስተውሏል ተብሏል። የተማሪዎች ፕሬዝደንትም ሆነ በግቢው ያለ የፌደራል ፖሊስ በዝምታ በማየታቸው ተደራጅተው በማደር የካቲት 24/2014 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ በድንጋይ እና በፌሮ በፈጸሙት ጥቃት 2 የአማራ ተማሪዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ጌታቸው የተባለ የ2ኛ ዓመት የአግሪ ተማሪ እና ተሾመ የተባለ የኬሚስትሪ ተማሪዎች በኮብል ስቶን በተፈጸመባቸው ድብደባ ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጧል። በግቢው ያሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት የአማራ ተማሪዎች በተደራጁ አካላት ሲደበደቡ ለመታደግ አልቻሉም ይልቁንስ ራሳቸውን ለመከላከል በሚሞክሩት ላይ ጥይት ሲተኩስና የጭስ ቦንብ ሲጥልና ሲያሳድድ ነበር ተብሏል። የተደራጀውን ጥቃት ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በዋቻሞ ግቢ ያሉ ከአስር ሽህ በላይ የአማራ ተማሪዎች በዋቻሞ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ ተነግሯል። በሀድያ ዞን ዋቻሞ አካባቢ የሀገር ሽማግሌዎች በመግባት ወደ ግቢ እንዲገቡ የጠየቋቸው ቢሆንም ዋስትና የሚሰጠን የለም በሚል በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸዋል። አብዛኞቹ ካፌ ላይ ችግር ለመፍጠር የተዘጋጁ ተማሪዎች አሉ በማለት ጾማቸውን እንደዋሉ ተናግረዋል። የሚመለከተው አካል አሁንም ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ተማሪዎቹ ጠይቀዋል። አሚማ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝደንት አድራሻ እንዳገኘ ምላሻቸውን በማካተት ተጨማሪ መረጃ ይዞ የሚመለስ ይሆናል። ፎቶ_Tabor press

Source: Link to the Post

Leave a Reply