በዋናነት በመተከል እና በሌሎችም አካባቢዎች በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት ፈጻሚዎችን ለማውገዝና በመንግስት ላይም ግፊት ለማሳደር ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ ለፊታችን እህድ…

በዋናነት በመተከል እና በሌሎችም አካባቢዎች በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት ፈጻሚዎችን ለማውገዝና በመንግስት ላይም ግፊት ለማሳደር ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ ለፊታችን እህድ…

በዋናነት በመተከል እና በሌሎችም አካባቢዎች በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት ፈጻሚዎችን ለማውገዝና በመንግስት ላይም ግፊት ለማሳደር ያለመ ሰላማዊ ሰልፍ ለፊታችን እህድ ታህሳስ 18 ቀን መጥራቱን የአማራ ወጣቶች ማህበር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሰላማዊ ሰልፉ በመላው የአማራ ከተሞች እንደሚደረግ የገለፀው ማህበሩ ሙሉ መግለጫውን ልኮልናል። መግለጫው የሚከተለው ነው። የአማራን ሕዝብ ማህበራዊ እረፍት ለመንሳት ከትናንት የቀጠለዉ በሕግና በመንግስት የተደገፈዉ የዘር ጭፍጨፋ ዛሬም ተባብሶ ቢንሻጉል ጉምዝ ክልል በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከ200 በላይ ንፁሃን አማራዎች በገጀራና በቀስት የሲቃ ድምፅ እያሰሙ ህይወታቸዉ አለፈ፤ መቃብራቸዉ በግሬደር ተሰብስቦ የጅምላ ሆነ። የደረሱልን ጥሪ ድምፅ እንደ እያሪኮ ጮኸ ዳሩ ግን በሕይወት የመኖር የተፈጥሮ መብታቸዉን የሚታደግ የመንግስት አካል ሊደርስላቸዉ ባለመቻሉ ህይወታቸዉ በመንግስት በሚደገፉ ሃይሎች አለፈ። የመተከል መሬት በደም ታጠበ አኬልዳማም ሆነ፣ ንፁሃን በላያቸው ላይ በር ተቆልፎባቸው በገዛ ቤታቸው እንደ ጧፍ ነደዱ፡፡ በሕገ መንግስት የተደገፈዉ አማራን ሀገር አልባ ያደረገዉ ህገ መንግሰታዊ ጭፍጨፋ ዛሬም በኦሮሚያ ክልል በምሰራቅ ወለጋ ንፁሃን አማራዎች በገጀራ ሕይወታቸዉ አልፏል፤ የድረሱልን ጥሪ የሚሰማበት መንገድ የለም። የሞታችን ዘግናኝነት በማይካድራ፣ በሁመራ፣ በቢንሻጉል መተከል ዞን እና በምሰራቅ ወለጋ በጅምላ መሆኑን ቀጥሏል፤ አሟሟታችን ከውሻ አነሰ፤ ሞታችን የሞት ሞት ሆነ። የተከበርከዉ የአማራ ሕዝብና ወጣት በግፍ ያልተጨፈጨፍከዉ መተከል ላይ ባለመገኘትህ እና የመተከል ነዋሪ ባለመሆንህ ነዉ። እናም በግፍ ወደ ጅምላ መቃብር ለወረደዉ ወገንህ ተቃውሞህን እንድታሰማ የፊታችን እሁድ ማለትም ታህሳስ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 በመላዉ አማራ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገዉ አሰቸኳይ ሰብሰባ ውሳኔውን አሳልፏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply