በዋግኸምራ ብሄረሰብ ዞን የተጠለሉ ዜጎች ወደ ቄያቸዉ መመለስ ጀምረዋል ተባለ።የአስተዳደሩ አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፥ ተጠልለዉ ከሚገኙ ከ…

በዋግኸምራ ብሄረሰብ ዞን የተጠለሉ ዜጎች ወደ ቄያቸዉ መመለስ ጀምረዋል ተባለ።

የአስተዳደሩ አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ፅህፈት ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፥ ተጠልለዉ ከሚገኙ ከ 90 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መካከል ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁት ዎች ወደ ቄያቸዉ እየተመለሱ ነዉ ብሏል፡፡

በዋግኸምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር 92 ሽህ 5 መቶ 91 ተፈናቃዮች ተጠልለዉ እንደነበር የአስተዳደሩ አደጋ ስጋትና ምግብ ዋስትና ሀላፊ አቶ ሰለሞን ንጉስ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አስታዉቀዋል፡፡

እነዚህ ተፈናቃዮች በጦርነቱ ምክንያት ተሰደው በዋግኸምራ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ለተፈናቃዮቹ የሰባዊ እርዳታ አቅርቦት እየደረሳቸዉ እንደሆነም አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ተፈናቅለዉ ወደ አካባቢዉ የመጡት ዜጎች ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ መደረጉንም ከአስተዳደሩ ሰምተናል፡፡

አሁን ላይ የዋግኸምራ የፀጥታ ሁኔታ አንጻራዊ ሰላም የሚታይበት መሆኑንም አቶ ሰለሞን ለ ኢትዮኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን

ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply