በዋግኽምራ ሰቆጣ በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ለ400 አባዎራዎች ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግ…

በዋግኽምራ ሰቆጣ በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ምክንያት ለተፈናቀሉ ለ400 አባዎራዎች ድጋፍ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የትግራይ ወራሪ ሀይል ከፍተኛ ግፍ ከፈፀመባቸው ቦታወች አንደኛው ዋግኽምራ ነው። የወሎ ቤተ አምሐራ የበጎ አድራጎት ድርጅት 450,000 ብር/አራት መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ወጭ የተደረገበት 100 ኩንታል የምግብ ዱቄት ለ400 አባዎራዎች አበርክቷል። ድጋፉም ለአንድ ቤተሰብ 25 ኪሎ ድቄት መሆኑ ተገልጧል። የመንግስት መዋቅር በወቅቱ ፈርሶ የነበረ በመሆኑ ህዝቡ ለከፋ ችግር እንዳይጋለጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት የዋግኽምራ ዞን አስተዳዳሪ አቡነ በርናባስ ባዋቀሩት አሰራር መሰረት ማህበሩ ድጋፍ ማድረግ ችሏል። ይሄ ስራ እንዲሳካ በገንዘብ የደገፉ በኔዘርላንድ /ሆላንድ/ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮ-ኔዘርላንድ የሰብዓዊ እርዳታ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በችግረኞች ስም ከልብ እናመሠግናለን ብሏል ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply