በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቁ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች እስካሁን አልተፈቱም ተባለ፡፡ከሰብአዊ ድጋፍ ውጪ ያሉት ድጋፎች በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አለ…

በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቁ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች እስካሁን አልተፈቱም ተባለ፡፡

ከሰብአዊ ድጋፍ ውጪ ያሉት ድጋፎች በዚህ ሁለት ወር ውስጥ ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸውን እና ችግሮቹም እንዳሉ ተነግሯል ፡፡

የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት በድርቁ ተጋላጭ ተብለው የተለዩ የማህበረሰብ ክፍሎች 4 መቶ 25 ሺ አንድ መቶ 30 ሰዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በደርቁ ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች በሁለት ዙር የእለት ምግብ ድጋፍ 51 ሺ 1 መቶ 86 ኩንታል እህል፤ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ደግሞ ዝቅተኛ ለአንድ ሰው በወር 410 ብር ከፍተኛ 7 ሺህ ብር ለ2 ሺ 7 መቶ 73 ሰዎች ሰብአዊ ድጋፍ መስጠት እንደቻሉ ጠቅሰዋል ።

ይህ ድጋፍ ላለፉት 7 ወራት በሁለት ዙር ብቻ የተሰጠ መሆኑን እና በ 5 ወራት ድጋፍ መስጠት አለመቻላቸውን አንስተዋል፡፡

እንደ አጠቃላይ ሲታይ ወደ 27 ፐርሰንት ብቻ ድጋፍ እንደተረገ ተናግረዋል፡፡

1 መቶ 71 ሺ የሚሆኑ እንስሳት ወደ አጎራባች ወረዳ ስደት እንደሄዱ እና እስካሁን አለመመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም በጥናት በተደገፈ መልኩ ጥያቆዎችን ብናቀርብም ካጠናነው የተጋላጭ ቁጥር ከ10 እስከ 15 ፐርሰንት ያልበለጠው ነው የሚፈቀድልን ብለዋል፡፡

በድርቅ የተጋለጡ እና የተጠቁ አካባቢዎች ተብለው የተለዩ ወረዳዎች ላይ ሳይቀር ከድርቁ በፊት ያገኙ ከነበረው ድጋፍ በታች እያገኙ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ይህም በአካባቢው ያለውን ችግር ካለመረዳት የመጣ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንትም በአበር ገሌ ወረዳ የኩፍኝ ወረሽኝ ተከስቶ 4 ሰዎች መሞታቸውን አቶ ምህረት ተናግረዋል፡፡

በርከት ያሉትን ደግሞ በጤና ተቋም ውስጥ በመረባረብ የመከላከል ስራ እየሰሩ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ሁሉም ሰው እንዲያግዘን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply