You are currently viewing በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚደረግላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ በምሬት ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም…

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚደረግላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ በምሬት ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም…

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በዝቋላ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች የሚደረግላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ በምሬት ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከዝቋላ ወረዳ ደብረፀሃይ /05 ቀበሌ/ በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው ቤት ንብረታቸውን ትተው ከመጡት መካከል ወይዘሮ ጥላዬ አፈማር እና አቶ ገብረኪሮስ በላይ እንደተናገሩት አካባቢያችን ላይ ጠላት ስለገባ ሀብት ንብረታችን ትተን ባዶ እጃችን ወጥተን መጣን ከመጣን ጀምሮ ግን የሚሰጠን እርዳታ በቂ አይደለም። የምንበላው ምግብ፣የምንለብሰው ልብስ፣የምንተኛበት ምኝታና የምግብ ማብሰያ እቃም የለንም በዚህ ምክንያት ልጆቻችን በርሃብ ሊሞቱብን ስለሆነ መንግስት እና የሚመለከተው አካል ችግራችን ተረድቶ ልጆቻችንን በሞት ሳንነጠቅ አሁንኑ ሊደርስልን ይገባል ሲሉ በምሬት ተናግረዋል። የዝቋላ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የጤና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ እስጢፋኖስ ወንዳዬ በበኩላቸው በመንግስትና አንዳንድ ግብረሰናይ ድርጅቶች አልፎ አልፎ ድጋፍ ያደረጋሉ ብለዋል። የስንዴ እርዳታም አንድ ጊዜ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲደርስ ብናደርግም ሁሉም ግን ሙሉ በሙሉ ያለውን ችግር ሊፈታልን አልቻለም በማለት ተናግረዋል። አቶ እስጢፋኖስ ወንዳዬ ጨምረው እንደገለጹት ለዚህ ለተራበ እና ለተራቆተ ህዝብ መንግስት ለችግሩ ቶሎ ሊደርስለት ይገባል የመጀመሪያው ስራ የሰላምና ደህንነቱ ጉዳይ ላይ ያሉ ችግሮች በዋናነት መፈታት አለባቸው ምክንይቱም ችግሩ ከተፈታ ይህ ተፈናቃይ ማህበረሰብ ወደ ቀየው ተመልሶ ከቤቱ ይገባል ለዚህም ሁላችንም በጋራ መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል ሲል ዋግኽምራ ኮሚዩኒኬሽን ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply