You are currently viewing “በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አሁን ላይ የተፈናቃይ ቁጥር ከ52 ሽ በላይ ደርሷል።” ሲል የዞኑ ኮምኒኬሽን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም…

“በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አሁን ላይ የተፈናቃይ ቁጥር ከ52 ሽ በላይ ደርሷል።” ሲል የዞኑ ኮምኒኬሽን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም…

“በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አሁን ላይ የተፈናቃይ ቁጥር ከ52 ሽ በላይ ደርሷል።” ሲል የዞኑ ኮምኒኬሽን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ ከዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽ/ቤት አጭር መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሠጡት የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ደስታዬ ጌታሁን ሲሆኑ መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል:_ እንደ ብሄረሰብ አስተዳደር አሁን ላይ የተፈናቃይ ቁጥር ከ52 ሽ በላይ ደርሷል። ከአበርገሌ፣ ከፃግብጅ፣ ከዛታ፣ ከኮረም እና ከአለማጣ ወረዳዎች እንዲሁም ከዝቋላና ከሰቆጣ ዙሪያ ወረዳዎች የተወሰኑ ቀበሌዎች በየቀኑ በአማካይ ሁለትሽ ተፈናቃዮች ይመጣሉ። በብሄረሰብ አስተዳደሩ ሦስት መጠለያዎች ተዘጋጅተው በዝቋላ መጠለያ ጣቢያ 18 ሽ 304 ፣ በወለህ መጠለያ ጣቢያ 10 ሽ 15 ተፈናቃዮች ተጠልለው ይገኛሉ። ከፍተኛው የተፈናቃይ ቁጥር በሰቆጣ መጠለያ ይኖራል። እስካሁን ድረስ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ነው ባይባልም ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ እረጅ ድርጅቶች ልዩ ልዩ የታሸጉና በዱቄት መልክ የተዘጋጁ አልሚ ምግቦች፣ የተለያዩ የምግብ ማብሰያ እቃዎች ፣ የጥራጥሬ እህሎች ፣የመኝታ፣ የመጠለያ እና የተለያዩ አልባሳት ለተፈናቃዮች ተሰጥተዋል አሁንም በመሠጠት ላይ ይገኛሉ ። በየጊዜዉ ከሚመጣው የተፈናቃይ ቁጥር አኳያ ሲታይ ብዙ ድጋፍ ስለሚያስፈልግ ቀጣይ ሀብት የማፈላለግ ስራ እንሰራለን። በዋናነት ግን ችግሩ በዘላቂነት ተፈትቶ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ወደየመጡበት አካባቢ ተመልሰው የቀደመ ኑሯቸውን በሰላም እንዲመሩ የሚደረግበት ሁኔታ ካልተመቻቸ ችግሩን የማንቋቋምበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን። በመሆኑም የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የጉዳዩን አሳሳቢነት በትኩረት ሊመለከቱት ይገባል ብለዋል። የካቲት 30/2014 ዓ.ም ሰቆጣ፣ ዋግ ኽምራ ኮሚዩኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply