በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ14 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸው ተነገረ፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በመኖ እጥረት 14 ሺህ 3 መቶ 97 እንስሳት መሞታቸውን የዞኑ አስተዳደር ጽፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በድርቁ ምክንያት በሶስት ወረዳዎች እና በ45 ቀበሌዎች ላይ 7 መቶ 91 ሺ የሚሆኑ እንስሳት ተጋላጭ በመሆናቸው ምክንያት ተለይቶተው እንደነበር ያስታወሱት፤ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽፈት ቤት ሃላፊ ምህረት መላኩ ናቸው፡፡

እንደ ሃላፊው ገለጻ፤ በመኖ እጥረት ምክንያት የተዳከሙ እንስሳት እንዳይሞቱ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል ብለዋል፡፡

በድርቁ ምክንያት ተጋላጭ የሆኑ እንስሳት ቁጥሮች ከፍተኛ በመሆኑ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉ ተጠቁሟል፡፡

በእሊኔ ግዛቸው

ሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply