በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሚገኙ ከ425 ሺህ በላይ ዜጎች  ሰብዓዊ እርዳታ የሚሹ ናቸው ተባለ

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ425 ሺህ  በላይ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳት የሚሹ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር ጽፈት ቤት አስታውቋል፡፡

54 በመቶ ለሚሆኑት የድርቁ ተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፎች መደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፤ 46 በመቶ ለሚሆኑት ተጋላጭ ዜጎች ይህን ማድረግ አለመቻሉን በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን
የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽፈት ቤት ሃላፊ ምህረት መላኩ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ላይ በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ተጋላጭ ለሆኑ ከ425 ሺህ በላይ ዜጎች መካከል፤ 54 በመቶ ለሚሆኑት ሰብዓዊ ድጋፎች መከናወኑ ተነግሯል።

222 ሺህ ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ከ3 ጊዜ በላይ የእለት ምግብ ድጋፍ መከናወኑ የገለጹ ሲሆን፤ ለተወሰኑት  የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን እና ለቀሪዎቹ የድርቁ ተጋላጮች ግን ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ መቸገራቸው ተጠቁሟል፡፡

መጪው የክረምት ወቅት እደመሆኑ እና በድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎች ላይ የከፋ ችግር እንዳይደርስ ከተለያዩ ድርጅቶች ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚሆኑ እርዳታዎችን መጠየቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

በእሌኒ ግዛቸው

ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply