በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ ቤላ አምባ የማህበረሰብ ጥብቅ ደን እሳት አደጋ አሁንም አልቆመም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲ…

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ ቤላ አምባ የማህበረሰብ ጥብቅ ደን እሳት አደጋ አሁንም አልቆመም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ቤላ ተራራ የእሳቱ መነሻ ያልታወቀው ሰደድ እሳት መጋቢት 03/07/14 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ገደማ የጀመረ ሲሆን ይህን ቃጠሎም አሁንም ድረስ ማስቆም አልተቻለም። በአስከተማ ገጽ የጀመረው ቃጠሎ በ4/07/14 ዓ.ም ወደ ሰቆጣና ቆብ ዝባ ገጽ በመዞር ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል። የአስከተማ ማህበረሰብ፣ ሚሊሻውና ልዩ ሀይሉ ከትላንት ጀምሮ እሳቱን ለማትጥፋት እየለፋ ቢሆንም ሰደድ እሳቱን ሊያስቆሙት አልቻሉም። ቦታው ገደላማና ወጣ ገባ በመሆኑ በሰው ሀይልም ሆነ በእሳት አደጋ መከላከያ መኪና መከላከል እንደማይቻልና በአውሮፕላን በታገዝ እንዳለበት በቦታው ላይ ያሉ የጋዝጊብላ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሌላ እንደአማራጭ የጋዝጊብላ ወረዳ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የሰቆጣና አጠቃላይ የዋግ ህዝብ ተረባርቦ ቤላን መታደግ የይሁንታ ሳይሆን ግዴታ ነው። ይህ ተራራ የዋግ የውሀ ጋን መሆኑ ሳይዘነጋ፣ የጥቅጥቅ ደን ባለቤት መሆኑ ሳይረሳ፣ በዙሪያው የምጣኔ ሀብት ማህደር እንደሆነና አያሌ ወጣቶች ንብ በማነብ የህይወታቸው መሰረት መሆኑን ልብ ብለን አይከፍሉት መስዋእትነት ተከፍሎ እሳቱ ሊጠፋ ይገባል ሲል የዋግ ኽምራ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply