በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጋዝጊብላ ወረዳ ንግድ ማህበረሰብ ዛሬም እንደትላንቱ ለወገን ጦር ” ለስንቅ አታስቡ እኛ አለን” በማለት ደጀንነቱን እያሳየ ነው። ነሐሴ 30/2014 ዓ…

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የጋዝጊብላ ወረዳ ንግድ ማህበረሰብ ዛሬም እንደትላንቱ ለወገን ጦር ” ለስንቅ አታስቡ እኛ አለን” በማለት ደጀንነቱን እያሳየ ነው። ነሐሴ 30/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በጋዝጊብላ ወረዳ የንግዱ ማህበረሰብ ሀገርን ለመውረር እና ለማፍረስ የመጣውን ሀይል ድባቅ ለመምታት በግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙ የሀገር ዋልታና ማገር ለሆነው የመከላከያ ሰራዊት ፣ሚሊሻና ፋኖ አባላት “ስንቅ አታስቡ እኛ አለን” በማለት ስንቅ በማዘጋጀት ለወገን ጦር ደጀንነቱን እያሳየ ይገኛል። የንግዱ ማህበረሰብ በራሱ አደረጃጀት አሸባሪው ሀይል የተከፈተብንን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ከእኛ ምን ይጠበቃል ብሎ በመምከር ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ በመወሠን በአንድ ቀን ከ110,000 ( አንድ መቶ አስር ሽ) ብር …በላይ በማዋጣት ጠላትን በሚፋጅ ክንድ እየደቆሶ ወደ መጣበት እያባረረ ለሚገኘው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ስንቅ በማቅረብ ዛሬም እንደትላንቱ ደጀንነቱን እያሳየ ይገኛል። የንግድ ማህበረሰብ ተወካይ እንደገለፁት እኛ ነግደን ማትረፍ፣ መበልፀግ የምንችለው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው ሰላም ከሌለ ሁሉም ነገር ዋጋ የለውም ሰላም ተፈጥሮ ወደ ልማት እንድንገባ ከእኛ የሚጠበቀዉን ከሎጅስቲክ እስከ ግንባር ድረስ ለመዋጋት ቁርጠኞች ነን ሲሉ የምንጊዜም ደጀንነታቸውን አረጋግጠዋል። አሁን እያደረግን ያለውን ድጋፍ በብዛትም ሆነ በአይነት በብዙ እጥፍ በመጨመር ድጋፋችን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ለጦምር ጦሩ ያላቸውን አጋርነት ገልፀዋል። © የጋዝጊብላ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply