በዌስት ባንክ ጥቃት ሊያደረስ ነበር የተባለ ፍልስጤማዊ በእስራኤል ወታደሮች ተገደለ፡፡

የ17 ዓመቱ አታላህ ሙሐመድ በወታደሮቹ ላይ በስለት ታግዞ ጥቃት ሊየደርስ ሲል ነው የተገደለው፡፡ በዌስት ባንክ በሚገኝ ኤሪዬል በተባለ የሰፈራ አካባቢ የተፈጠረው የጥቃት ሙከራና ግድያ በፍልስጤም ባለስልጣናት የተረጋገጠ ነው፡፡

ሆኖም ወጣቱ መሳሪያ የታጠቁ ወታደሮችን በስለት ለማጥቃት የሄደበት ርቀት አለመረጋገጡ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡ በእርግጥ የእስራኤል ወታደሮች ከዚህ በፊት በርካታ የጥይትና የስለት ጥቃቶች ሲደርሱባቸው እንደቆዬ ይነገራል፡፡ጥቃት አድራሾቹም በህገ-ወጥ ሰፈራዎች ምክንያት የሚበሳጩ ወጣት ፍልስጤማውያን ናቸው፡፡

የፍልስጤምና የእስራኤል የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን ዛሬም ድረስ ከተገቢው በላይ የሆነ ሃይልን ይጠቀማል በሚል የእስራኤልን መንግስት እንደሚከሱ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግባል፡፡

************************************************************************

ቀን 19/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በዌስት ባንክ ጥቃት ሊያደረስ ነበር የተባለ ፍልስጤማዊ በእስራኤል ወታደሮች ተገደለ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply