በውጪ ሆነው የሚጽፉ የትግራይ ተወላጆች ፍላጎት በክልሉ በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ   ( አሻራ ፣ የካቲት 16/06/ 13 ዓ.ም ባህር ዳ…

በውጪ ሆነው የሚጽፉ የትግራይ ተወላጆች ፍላጎት በክልሉ በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ ( አሻራ ፣ የካቲት 16/06/ 13 ዓ.ም ባህር ዳ…

በውጪ ሆነው የሚጽፉ የትግራይ ተወላጆች ፍላጎት በክልሉ በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተናገሩ ( አሻራ ፣ የካቲት 16/06/ 13 ዓ.ም ባህር ዳር) በውጪ አገራት ተቀምጠው ስለ ትግራይ ክልል ሁኔታ የሚጽፉ የትግራይ ተወላጆች ፍላጎት ለትግራይ ሕዝብ የመድኃኒትና የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ ደርሶ ከችግር መታደግ ሳይሆን፣ የትግራይ ሕዝብ በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ሲሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቦቹን ከ15 ያልበለጡ እንደሆኑ ነው የማውቀው ያሉት አቶ አንዳርጋቸው፣ እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ በየትኛውም ድርጅትና ሕዝብ ዓይን ቦታ የሚሰጣቸው አይደሉም፣ ከዚህ በመነሳት ዲያስፖራው በሙሉ እንዲህ ዓይነት አሳፋሪ ተግባር ይፈፅማል ለማለት አልደፍርም፣ ተደማጭነት አላቸውም ብዬ አላምንም ብለዋል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው በዚህ ሰዓት ላይ እነሱ የሚፈልጉት ነገር ግልፅ ነው፣ የሚፈልጉት ለትግራይ ሕዝብ ጭራሹኑ የመድኃኒትና የምግብ እርዳታ በአስቸኳይ ደርሶ ከችግር መታደግ ሳይሆን፣ የትግራይ ሕዝብ በሚሊዮኖች የሚያልቅበት ሁኔታ እንዲፈጠር ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት ሕዝባችንን አስጨረሰ የሚል የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት ነው ያሉት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ይህ አካሄዳቸው የተለመደና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያለ የኢትዮጵያ ሊሂቃን የትግል አቅጣጫ እንደሆነና የዚህ ዓይነት አመለካከት በእኛ አገር ስር የሰደደ መሆኑን አክለዋል፡፡ አቶ አንዳርጋቸው የሰው ሕይወትን ያህል ነገር ለፖለቲከኛው ወደ ግቡ መድረሻ ቁማር ሆኖ ነው የቆየ ነው በማለት ፖለቲካችን በዚህ መልኩ የተቃኘ ነው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply