በውጭ መረጃ ተቋማት የሚነዛው የተሳሳተ መረጃ የደህንነት ስጋት ሆኗል ተባለ

የውጭ የመረጃ ተቋማትና ዓለም አቀፍ የሽብር ድርጅቶች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚያሰራጩትና የሚነዙት የሀስት ወሬ እየሰራ ይመስላል ያሉት፣ አንድ ከፍተኛ የሃገር ውስጥ ደህንነት ባለሥልጣን፣ ይህም በመጭዎቹ ሳምንታት ውስጥ የሽብር አደጋን ሊያስከትል ይችላል የሚል አዲስ ሥጋት ማሳደሩን ተናገሩ፡፡

ባላፈው ኅዳር ታትሞ ከወጣው የፀረ ሽብር ጥናታዊ ዘገባ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው የተነገረለት ይህ ማስጠንቀቂያ የወጣው፣ የገና በዓልና አዲስ ዓመትና እንዲሁም አንደኛ ዓመቱን ከሚይዘው፣ እኤአ ጥር 6 ቀን በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ የተካሄደው የወረራ ጥቃት በሚታሰብበት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አክራሪነትን አስመልክቶ ትናንት ረቡዕ በተዘጋጀው ፎረም ላይ የተናገሩት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ደህንነት ሚኒስትሩ ከፍተኛ ባለሥልጣን ጆን ኮኸን “ሥጋቱ ይበልጥ አደገኛና ተለዋዋጭ” ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል፡፡

ሽብርተኝነትን በመቋቋም “መሻሻል አሳይተናል፡፡ አሁንም ዕለት ተዕለት መሻሻላችንን ቀጥለናል፡፡” ያሉትን ባለሥልጣኑ ይሁን እንጂ “አሁንም ገና ብዙ ይቀረናል” ብለዋል፡፡ 

ባለፈው ኅዳር የወጣው የጸረሽብር ዘገባ ዩናይትድ ስቴትስ እኤአ በቀረው እአአ 2021መጠናቀቂያና በሚቀጥለው አውሮፓ 2022 ዓመት መግቢያ ላይ ከሃገር በቀል አክራሪዎች  የሽብርተኝነት አደጋ ሊገጥማትእንደሚችል ያለውን ሥጋት አመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ አክራሪነትን አስመልክቶ በተደረገው በትናንቱ ውይይት የውጭ መንግሥታት የመረጃ ተቋማት በሚያደርጓቸው በርካታ ተግባራት ጉዳዩን ያወሳሰበው መሆኑን ባልሥልጣኑ ተናግረዋል፡፡ 

ብዙዎቹ በዘመቻ መልክ ከውጭ ያለ ማቋረጥ የሚነዙ እጅግ የተወሳሰቡ የሀሰት መረጃዎች እንደሚደርሷቸውም ገልጸዋል፡፡

ኮሆን እነዚህ የተሳሳቱ መረጃዎች ከማህበራዊ ሚዲያውም አልፈው የዋና ዋና ዜና አውታሮችን ትኩረት የሚያገኙበት የተወሳሰበ መንገድ አላቸው ብለዋል፡፡

የተዛቡ ወሬዎች ለብዙዎች ሰዎች በደረሱና ብዙዎችም በተቀባበሉት ቁጥር ከዚያ መካከል በሰሙት ነገር የሚነኩ ወይም በመቆጣት ተነስተው ላልሆነ ተግባር የሚገፋፉ ሰዎች መኖራቸው ተብራርቷል፡፡ 

የሃገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሩ አሌጃንድሮ ማዮርካስም ባላፈው ማክሰኞ ይህ ሥጋት የመነጨው እየተነዛ ከሚገኘው የሀሰት ኢንፍሮሜሽን ዘመቻ ውጤት የተነሳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

“የተሳሳተ ወሬ ዘመቻ የደህንነታችን ሥጋት ምንጭ ሆኗል”  ብለው መናገራቸውምተዘግቧል፡፡

ቻይናና ኢራን፣ የሩሲያን ፈለግ ተከትለው፣ የሃገር ውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችን በመጠቀም፣  የተሳሳተ ኢንፍሮሜሽን እንደሚነዙ ተነግሯል፡፡

በዚህም በተወሰነ መልኩ የተሳካ ሥራ መስራታቸውንም የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የሚያምኑ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የአሜሪካውያን ከማህበራዊ ሚዲያዮች ጀምሮ የሚሰሟቸውን የዜና የመረጃ ምንጮች ምንነት በትክክል እንዲገነዘቡ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply