በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተካሄደ

በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በስብሰባው የቅንጅት መድረኩ አስፈላጊነት፣ የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ እያደረጉ ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎችና የችግሮቹን አፈታት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በስብሰባው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ የድህረ ኢንቨስትመንት ክትትልን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በሃገር ውስጥ በኢንቨስትመንት ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ ባለሃብቶችን ማቆየት፣ ማስፋፋትና ትስስር መፍጠር የሚችሉበትን አሰራር በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ነባራዊ ሁኔታ የሴክተር መስሪያ ቤቶች የራሳቸውን ተቋም ብቻ ትኩረት ማድረግና የመቀናጀት ውስንነት መኖሩ ተነስቷል።

ከዚህ ባለፈም የኢንቨስትመንት መመሪያ የመረዳትና ባለሃብቶችን የመቀበል ችግሮች መኖራቸው እንዲሁም የኮቪድ-19 ተጽዕኖ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠሩም በጥናታዊ ፅሁፉ ተጠቅሷል፡፡

ውይይቱን ተከትሎ በአጠቃላይ የቅንጅት መድረኩን የጋራ ተግባራት በማጠናከር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በስፋት መሳብ እንደሚያስፈልግና በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተካሄደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply