
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአዲስ አበባው የዒድ ሰላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር በግንባር ቀደምነት የተሳተፉ 76 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ። ግብረ ኃይሉ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፣ “የሁከትና ብጥብጥ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ለብጥብጥ መነሻ በማይሆን ምክንያት” ከስታዲየም ውጭ በተለምዶ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም አጠገብ ሆነው ባስነሱት ረብሻና ብጥብጥ በጸጥታ ኃይሎችና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልጿል።
Source: Link to the Post