በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይቀርብ የነበረ ዕርዳታ በመንግሥት ሊመራ ነው፡፡የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ የዕርዳታ ሥርጭትን እንደሚቆጣጠር አስታዉቋል፡፡የፌዴራል መ…

በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይቀርብ የነበረ ዕርዳታ በመንግሥት ሊመራ ነው፡፡

የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ላይ የዕርዳታ ሥርጭትን እንደሚቆጣጠር አስታዉቋል፡፡
የፌዴራል መንግሥት የሽሬ፣ ኮረምና አላማጣ ከተሞችን መቆጣጠሩን ካስታወቀ በኋላ፣ በሰሜን ጎንደር ወደ ሽሬ የሚወስደው መንገድና ከኮምቦልቻ ተነስቶ በደሴ-ወልድያ-ቆቦ ወደ አላማጣ የሚያደርሰውን መንገድ እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡

ይህም ከዚህ ቀደም በምድር ብቸኛ የነበረውን የአፋር የዕርዳታ መስመር ወደ ሦስት ያሳድገዋል፡፡
በተጨማሪም መንግሥት የሽሬ አውሮፕላን ማረፊያን በመጠቀምም ዕርዳታ እንደሚያቀርብ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ አስታውቆ ነበር፡፡

የአገልገሎቱ ሚኒስትር ዶ/ር) ለገሰ ቱሉ ‹‹በተረጂዎች ስም የሚመጣ የዕርዳታ እህልና መድኃኒት በየትኛውም የሽብር ቡድን እንዲዘረፍ መንግሥት አይፈቅድም›› በመሆኑም፣ መንግሥት የዕርዳታ ሥርጭቱን ይቆጣጠራል ማለታቸዉን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
የዕርዳታውን ሥርጭት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆኑ ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ›› እንደሆነና ተግባራዊነቱም በሁሉም አገሪቱ ክፍሎች መሆኑን አስፍረዋል፡፡
በትግራይ ክልል ዕርዳታ እያቀረቡ የነበሩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጦርነቱ በድጋሚ ካገረሸ በኋላ ሥራቸውን ለማከናወን አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳጋጠማቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ መቆየታቸዉ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን
ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply