በዓለም አቀፍ ገበያ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችሉ ምርቶችን ወደ ገበያው ለማስገባት ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ነው፡፡
ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ቡናን ጨምሮ ከ23 በላይ የግብርና ምርቶችን ወደ አለም ገበያ ሲያቀርብ መቆየቱን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ዳዊት ሞራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እስካሁን ድረስ የመጣበት መንገድም በግብርና ምርቶች ላይ ብቻ የተወሰነ ነበር ያሉት ዳይሬክተሩ፣ አሁን ላይ የኢንዱስትሪ ግብዓት ምርቶችንም ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸውልናል፡፡

በተጨማሪም በሲሚንቶ እና በማድናት ግብይት ላይ ያሉ ችግሮችን አስቀድሞ በጥናት የመለየት ስራ ተቋሙ እየሰራ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

እየተደረገ ያለው ጥናት በዚህ አመት ይጠናቀቃል ያሉም ሲሆን፣ ከጥናቱ በኋላ የተባሉት ምርቶች ወደ ገበያ እንደሚገቡ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ለሁሉም የምርት አይነቶች የሚሆን የዲጅታል የግብይት ስርዓት እየተዘረጋ በመሆኑ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በግብርና ምርቶች ብቻ አይገደብም ነው ያሉት፡፡

ከተመሰረት 15 አመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ በግብርና ምርት የግብይት ሰንሰለት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በተወሰነ ደረጃ ቢያስቀርም አሁንም ራሱን በሚገባ በመፈተሽ ከዘመኑ ጋር ሊራመዱ የሚችሉ አሰራችን መዘርጋት እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply