በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ’በቃ' ወይም '#NoMore' ዘመቻ አካል የሆነው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በእየሩሳሌም ተካሂዷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም…

በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆነው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በእየሩሳሌም ተካሂዷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሀገረ እስራኤል የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዓለምዐቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ’በቃ’ ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል የሆነውን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ኢየሩሳሌም ከሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት አካሂደዋል፡፡ በዚህም ኤርትራዊያን ተገኝተው በመሳተፍ አጋርነታቸውን ገልፀዋል። በወቅቱ ሰልፈኞቹ ባሰሙት መፈክር የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ አገራት በተለይም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ያልተገባ ጫናና ጣልቃ ገብነት አውግዘዋል። አሸባሪው ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች የፈጸማቸውን ግፍና በደሎች እንዲቆም የሁሉም ርብርብ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል። አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የፈጸማቸው እኩይ ድርጊቶች በወንጀል የሚያስጠይቁ እንደሆኑና ይህን ግፍና በደል በዝምታ ማለፍ ተገቢ አለመሆኑን አስገንዝበዋል። ምእራባውያን የኢትዮጵያውያንን ድምፅ እንዲሰሙና የአሸባሪው ትህነግ ድርጊት በማውገዝ ለፍርድ እንዲቀርብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ ሰልፍ ‘ኢትዮጵያ ታሸንፋለች፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ጎን ቆመናል” የሚል መልዕክት መስተጋባቱም ተገልጧል። የሰልፉ አስተባባሪ እና የቀድሞ የእስራኤል ፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ሽሎሞ ሞላ ባሰሙት ንግግር “እኛ በእስራኤል አገር ያለን ቤተ-እስራኤላዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ኢትዮጵያ ትውልድ አገራችን ናት፣ ኢትዮጵያ የትውልድ አገራችን ናት ስንል አያት ቅድመ-አያቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው ያቆሟትና እትብታችን የተቀበረባት ስለሆነ ኢትዮጵያ በልባችን ውስጥ ናት” ብለዋል። በተጨማሪም “ትውልድ አገራችን ኢትዮጵያ ስትነካ ቁጭ ብለን አናይም በማለት ነው የወጣነው፤ ይህንንም ስናደርግ ለእውነት እና ለፍትህ ስንል በትልቅ ፍቅርና በትልቅ ተስፋ ለኢትዮጵያ ሰላም የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፤ እንደዜግነታችን የእስራኤልን መንግስት ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ጎን እንዲቆም ጥሪ እናደርጋለን” ብለዋል ያለው በሀገረ እስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply