You are currently viewing በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማኅበር በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ዙሪያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ዕርዳታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     የካቲት 12 ቀ…

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማኅበር በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ዙሪያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ዕርዳታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀ…

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቅድስት ሥላሴ ልጆች ማኅበር በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ዙሪያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ዕርዳታ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሻሸመኔ ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ምዕመናን ላይ በሕገ ወጥ መልኩ የተሾሙ ግለሰቦች ባስነሱት ብጥብጥ እና በእነርሱ አቀነባባሪነት በተወሰደው የግፍ እርምጃ ለተጎዱ ወገኖች በሀዋሳ ከተማ በአላቲዎን እና ያኔት ሆስፒታል በመገኘት የጉዳት መጠናቸውን ተመልክቶ የአንድ ሚሊየን ብር (1,000,000 ) ድጋፍ አድርጓል። በሀገረ ስብከቱ በኩል ለተዋቀረው የዕርዳታ ኮሚቴም 450,000 ብር ድጋፍ አድርጓል። በጸጥታ ኃይሎች እና ወረበሎች በግፍ በአጣና ተቀጥቀጠዉ በሰማዕትነት ላለፉት ለቄስ ሐረገወይን ባለቤት የሁለት መንታ ልጆች እናት ምንም እንኳን በቂ ባይሆንም ለጊዜዉ ለችግር መሸፈኛ የሚሆን የ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ) ብር ድጋፍ አድርገዋል። በድምሩ ለ25 ሰዎች የ350,000 (ሶስት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) ገቢ አድርገዋል፤ የዕርዳታው አስተባባሪዎች ይህ ገንዘብ ለሰዉነት መጠገኛ የምግብ እና የመሳሰሉትን ጥቃቅን ነገር ይሸፍንላቸዋል ብለዋል። በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ክልል ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ እና የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሆስፒታል ተኝተው ህክምና የሚከታተሉ ወገኖችን ጎብኝተው አጽናንተዋቸዋል ። ጉዳቱ ከደረሰበት ጀምሮ ምግብ በማቅረብና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ለተባበሩ ለሀዋሳ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናንም ብፁዕነታቸው ታላቅ ምሥጋና አቅርበዋል። መረጃው፦ የኢኦተቤ ቲቪ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply