በዓለም የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር 71 ሚሊዮን ደረሰ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-6115-08db5257f151_tv_w800_h450.jpg

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር፣ እስከ ዛሬ ታይቶ በማያውቅ ደረጃ አሻቅቦ 71 ሚሊዮን መድረሱን፣ በኖርዌይ የስደተኞች ምክር ቤት፣ የተፈናቃዮችን ኹኔታ የሚከታተለው ንዑስ ክፍል ይፋ ያደረገው ሪፖርት አመለከተ።

ያለፈው ዓመት ተደራራቢ ቀውስ፣ በዐሥር ሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሰዎችን ከአገራቸው እንዲሰደዱ ማስገደዱን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ በተለይ በዩክሬን ያለው ጦርነት፣ የተፈናቃዮች ቁጥር በብዛት እንዲጨምር ማድረጉን ጨምሮ አስታውቋል።

ዘገባው የአሶሽየትድ ፕሬስ እና የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply