በዓሉ እርስ በእርስ የምንተሳሰብበትና ከገጠሙን ችግሮች በጋራ ለመሻገር የምንደጋገፍበት እንዲሆን እመኛለሁ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ታላቁ የመውሊድ በዓል እርስ በእርስ ከልብ የምንተሳሰብበት፤ ከገጠሙን ችግሮች በጋራ ለመሻገር የምንደጋገፍበት እንዲሁን እመኛለሁ” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለ1495ኛው የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም “ለነቢዩ መሐመድ 1495ኛው ልደት በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ እንዲሁ ሁላችንንም አብሮ አደረሰን ለማለት እወዳለሁዕ ብለዋል።

“በታላቁ የመውሊድ በዓል እርስ በእርስ ከልብ የምንተሳሰብበት፤ ከገጠሙን ችግሮች በጋራ ለመሻገር የምንደጋገፍበት እና ከመላው የሃገራችን ህዝቦች ጋር ህብረታችንን የምናጠብቅበት እንዲሆን እመኛለሁ” ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

The post በዓሉ እርስ በእርስ የምንተሳሰብበትና ከገጠሙን ችግሮች በጋራ ለመሻገር የምንደጋገፍበት እንዲሆን እመኛለሁ ም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

This Post Has One Comment

Leave a Reply