በዓልን አስመልክቶ በሸቀጦች እና ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተነግሯል

በዓላት ሲመጡ የምርት ፍላጎት የሚጨምር ሲሁን፤ ይህን ተከትሎ የምርት እጥረት እንዳይከሰት በእሁድ ገበያዎች ላይ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ምርቶች እና መሰረታዊ ሸቀቶች እየተሟሉ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በተገነቡ 26 የገበያ ማዕከላት እና ከ170 በላይ በእሁድ ገበያ ምርቶች እና የሸቀጦች እጥረት እንዳይኖር ባለሞያዎች ተመድበው የተጠናከረ ቁጥር እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ምርቶች ተከዝነው በተገኙ ላይ ድንገተኛ ፍተሸ እንደሚከናወን እና የዋጋ ጭማሪ እና ያለ ደረሰኝ በሚያገበያዩ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ በቢሮው የክትትል ስራ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡ በመሆኑም በህገወጥ ንግድ ላይ በሚሰማሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቁሟል፡፡

በዓልን አስመልክቶ የዋጋ ጭማሪ እና የምርት እጥረት እንዳይከሰት ከደንብ ማስከበር፣ ከምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የግብረኃይል በማቋቋም ከከተማ እስከ ወረዳ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ህብረተሰቡ በምርቶች እና መሰረታዊ ሸቀቶች ላይ የዋጋ ጭማሪዎችን ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴችን ካስተዋሉ ለቢሮ እንዲያመለክቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

እሌኒ ግዛቸው
ሚያዝያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply