በዘመን መለወጫ በዓል ምንም አይነት የእሳት አደጋ አልተከሰተም!የ2015 ዓ.ም አዲስ አመት ያለምንም የእሳት አደጋ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/FFRruCBW3HoAH2Fb_DZJ4_0ISXf7Bg6hqXQB5HavgBzGeunxSQ_1-KHksIrntrIUfBBQr7OOgYJccXbeNinm8Bn_8OGEI9Yku8vWo1vgkGf0L94wLByAkgKO60o1OyM0iAt5nkmtrA52YgGNnMsHMYhvBCtrLlPgORxR_Hed4uSLg5dHCbYpC2YtMY_QO1zzDyhG4wl3Sa24xZu2AseEauRnad8UpkbdvoHgTzMxqWa0uUeFRf5Hr9rrUna5Sf45Px49sS6BkLrxrvOb6enhmYteYFoFuqv--hWyS_au75FyUl1Xug2Y-AR40MmtQ81-dfzw9xUoDoQlq0cMIF_pkw.jpg

በዘመን መለወጫ በዓል ምንም አይነት የእሳት አደጋ አልተከሰተም!

የ2015 ዓ.ም አዲስ አመት ያለምንም የእሳት አደጋ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከበዓላት ውጪ ባሉ በመደበኛ ቀናቶች በ24 ሰዓታ ዉስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ አደጋዎች እንደሚከሰቱ አስታዉሰዋል፡፡

ነገር ግን አደጋ ይበዛል ተብሎ በሚታሰብበት የበዓል ሰሞን በማህበረሰቡ እገዛ ሰላማዊ ሆኖ ማለፉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ይህ በዓል በ2014 ከነበሩ በአላት ሁሉ ከድንገተኛ አደጋ የጸዳ ሰላማዊ ሆኖ ማለፉን አመልክተዋል፡፡

ኮሚሽኑም በበዓሉ መሰል አደጋዎች እንዳይፈጠሩ በራሪ ወረቀቶችን ሲበትን እና ከሚዲያ ተቋመት ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ በ2014 ዓ.ም 115 ሰዎች በእሳት እና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ህየወታቸውን እንዳጡ የገለጹት አቶ ንጋቱ፤2015 ከአደጋዎች ሁሉ የጸዳ ሰላማዊ አመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

መስከረም 02 ቀን 2015 ዓ.ም

ለወቅታዊና ታማኝ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናላችንን ይከታተሉን!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply