በዘር አጥፊው የትሕነግ ቡድን ተደራራቢ ግፍና በደል ሲደርስባቸው የቆዩትና ዛሬ ላይ በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ነጻ የወጡት በወልቃይት ጠገዴ የአዲ ረመጥ ከተማ ነዋሪዎች በነገው እለት ሰ…

በዘር አጥፊው የትሕነግ ቡድን ተደራራቢ ግፍና በደል ሲደርስባቸው የቆዩትና ዛሬ ላይ በተከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ነጻ የወጡት በወልቃይት ጠገዴ የአዲ ረመጥ ከተማ ነዋሪዎች በነገው እለት ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንደገለፀው የአዲረ መጥ ከተማ የማፊያው ትሕነግ ከፍተኛ ጭቆና እና አፈና ካረፈባቸው የወልቃይት ጠገዴ አካባቢዎች አንዱ ነው። አማራዊ ማንነቱን በማፈንና አፅመ እርስቱን ተነጥቆ ለበርካታ ዓመታት በስቃይ እና እንግልት የኖሩት የአዲ ረመጥ ከተማ ነዋሪዎች የአማራ ልዩ ሀይል፣ፋኖ፣ሚሊሻና የመከላከያ ሰራዊት በከፈለው መስዋዕትነት በቅርቡ ነጻ መውጣታቸው ይታወሳል። የአዲ ረመጥ ከተማ የአካባቢው ነዋሪዎች በነገው እለት በሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ መልዕክቶች እንደሚስተጋቡ ይጠበቃል። የፀጥታ መዋቅሩና ህዝቡም በመናበብ ህዝቡን በሰላም እንዲያጠናቅቅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መስራት ግድ የሚል መሆኑ ግልፅ ነው። ነጻ በወጡ በርካታ የወልቃይት ጠገዴ አካባቢዎች ደማቅና ፍፁም።ሰላማዊ የሆኑ ህዝባዊ ሰልፎች መካሄዳቸው አይዘነጋም። በተደረጉት ሰልፎችም በተከፈለው መስዋዕትነት ነጻ ወጥተናል፤ እኛ አማራዎች ነን፤ የምንተዳደረውም በአማራ ክልል ነው፤ የሚሉ መልዕክቶች ጎልተው ተላልፈውበታል። ፎቶ:Central Gondar Communication

Source: Link to the Post

Leave a Reply