“በዘንድሮው ዓመት በጀት ውስጥ ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ለብድር የምከፈል ነው።“፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 309 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰብስቧል

ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከ2014 ዓመት በጀት ውስጥ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ወይም ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ለብድር የሚከፈል መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አገራዊ እዳን በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራርያ፤ በዘንድሮው በጀት ዓመት ውስጥ ከ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ወይም ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ለብድር ክፍያ የተመደበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አገራዊ ብድር በወቅቱ ሳይከፈል ከቆየ በጣም ከባድ ችግር ይዞ እንደሚመጣ ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ከዘንድሮው በጀት ከፍተኛ ገንዘብ ለብድር የሚከፈል ይሆናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 330 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር አውስተው፤ 309 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰሰቡን ተናግረዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ከ50 ቢሊየን ብር በላይ ጭማሬ ማሳየቱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰጡት ማብራሪያ ያስረዱት፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply