በዚህ ሳምንት በኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ለግንባታው ዘርፍ ዋነኛ ግብአት የሆነው የሲሚንቶ ገበያ እየታመሰ ነው፡፡ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የሲሚንቶ ፍላጎት ተፈጥሮ የምርቱ ዋጋ…

https://cdn4.telesco.pe/file/iL60BWgX9njZpobBgppB-vK7qIa2YnDOh8-NMjS_5J8rPDKvoKBiGKSV6WAm0UWx9RWXi-2GLbjRxDX3Is7oHlw9nMDd3IImNyD-ENm6saAnDbZy5OsP1BZJA7afi6YshxVUUgdf6Ad8ydgioiQFwjqjTpSNzseKrSi2PvqsaQQ4hUa-Pd0CPdYUZe-734E9A9iPzo_SWsDJDLBdKysp62JSLOTiUj6rQ_LPoDz2efgIlqAc88DcAZaTXFzIYoMeK5gacPhxmbURj9ksjqL5YU-f1nkDQv19o3o-wKs53M_sNzUpBrc85tTUaULxcbtM62-zQbTlsesbhh_aOCB6Sw.jpg

በዚህ ሳምንት በኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ

ለግንባታው ዘርፍ ዋነኛ ግብአት የሆነው የሲሚንቶ ገበያ እየታመሰ ነው፡፡ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የሲሚንቶ ፍላጎት ተፈጥሮ የምርቱ ዋጋ ጣሪያ ነክቷል፡፡በሀገሪቱ ካሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች አንዱ በሆነው የደርባ ሲሚንቶ ፋብሪካ ላይም ደባ ተፈጽሟል ፡፡የሲሚንቶ ዋጋ እንዲንር፤ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚቀርበው ሲሚንቶ እንዲስተጓጎል ሸፍጥ ተሰርቷል፡፡

በሌላ በኩል የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሁለተኛ የፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡

በእነዚህ እና ሌሎችም የሲሚንቶ ፖለቲካ ገጽታዎችን በዚህ ሳምንት የውይይት ሰአታችን ላይ እንነጋገራለን፡፡

እንግዳችን የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአት ኢንደስትሪ ልማት ኢኒስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሃላላ ናቸው::

ቅዳሜ ጠዋት በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ላይ ከ3፡00 – 4፡00 ሰዓት ያድምጡን!

ኢትዮ የንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ ኦሪጅንስ ሚዲያ ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ጋር በመተባበር ያቀርብላችኋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply