በዛሬው ዕለት በኢድ ሶላት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም…

በዛሬው ዕለት በኢድ ሶላት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ/ም የኢድ ሶላት ከመሰገዱ በፊት በሰማዕታት ሀውልት አካባቢ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ምዕመኑ አሁን ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ በመረጋጋት ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል። በቀጣይ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply