በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የከተማችን ዜጎች ለ 10 ወራት የሚቆይ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑን ሰምተናል በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነታቸው ያደረጉ 350ሺህ የሚጠጉ በዝቅተኛ የኑሮ…

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የከተማችን ዜጎች ለ 10 ወራት የሚቆይ የገንዘብ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑን ሰምተናል

በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነታቸው ያደረጉ 350ሺህ የሚጠጉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ወርሃዊ ድጋፍ ሊደረግላቸው መሆኑ ከሃላፊው ሰምተናል

የአዲስ አበባ ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደዳስታወቀው በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ 350 ሺህ ያህል ዜጎች ድጋፍ ሊያደርግ እንደሆነ ነግሮናል።

ድጋፉ ለሚቀጥሉት አስር ወራት የሚቆይ ሲሆን በየወሩ የአንድ ሺህ ብር ድጋፍ ያገኛሉ ብሏል፡፡

የምግብ ዋስትና ጽ/ ቤት የህብረተሰብ ተሳትፎ እና አደረጃጀት የቡድን መሪ አቶ ብርሀኑ ረዳ እንደተናገሩት ለዚህ መርሀ ግብር ማስፈጸሚያ የሚሆን 1 ቢሊየን 51ሚሊየን ብር ከአለም ባንክ በኩል መገኘቱን ነገረውናል ፡፡

በ350ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ ካደርጋል በተባለለት በዚህ መርሃ ግብር እስከ አሁን በሁሉም ክፍለ ከተሞች ደረጃ 290ሺህ ያህል ዜጎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡

ቀሪዎቹን 60 ሺህ የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ዜጎች የመለየቱ ስራ ደግሞ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ አቶ ብርሀኑ ነግረውናል

ሔኖክ ወ ገብርኤል
የካቲት 17 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply