በየመን የስደተኞች ጣቢያ በእሳት አደጋ ከሠላሳ በላይ ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተነገረ አሻራ ሚዲያ የካቲት /29/06/ 2013  ባህር ዳር በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በሚገኝና በርካታ ኢትዮጵያ…

በየመን የስደተኞች ጣቢያ በእሳት አደጋ ከሠላሳ በላይ ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተነገረ አሻራ ሚዲያ የካቲት /29/06/ 2013 ባህር ዳር በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በሚገኝና በርካታ ኢትዮጵያ…

በየመን የስደተኞች ጣቢያ በእሳት አደጋ ከሠላሳ በላይ ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተነገረ አሻራ ሚዲያ የካቲት /29/06/ 2013 ባህር ዳር በየመን ዋና ከተማ ሰንአ በሚገኝና በርካታ ኢትዮጵያውያን ታጉረውበታል በሚባል የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ በእሳት አደጋ ሰበብ ከሠላሳ በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ 170 ሰዎች ጉዳት እንዳስተናገዱ ቢቢሲ አፍሪካ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ባለሥልጣናትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡ በደረሰው አደጋ ከተጎዱት 170 ሰዎች መካከል 90 ያህሉ ጉዳታቸው ከፍተኛ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የመካከለኛው ምሥራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ዳይሬክተር ካርሜላ ጎድዮ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ … ዳይሬክተሯ የሚመሩት ድርጅት ለተጎጂዎቹ አስቸኳይ የሕክምና ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ ጨምረው አሳውቀዋል፡፡ ለእሳት አደጋው መነሻ ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያለው ነገር የለም፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ድረስ የኢትዮጵያ መንግስት ህይዋታቸው ስላለፉት ኢትጵያዊያን ዝምታውን መርጧል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply