በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ሀውቲን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ልንገትረው አቅደናል አሉ፡፡

ባለፈው መጋቢት 7 2021 እ.አ.አ በየመን መዲና ሰንዓ የሀውቲ ታጣቂዎች በርካታ ኢትዮጵያዊን በነበሩበት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተነሳ እሳት ብዙዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ በተለይም ከኢትዮጵያ የሄዱ ስደተኞች በተጠለሉበት በዚህ ስፍራ የተነሳው እሳት የሀውቲ ታጣቂዎች በሚሳኤልና በድሮን ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ ባለ ነዳጅ ማከማቻ መሞታቸውን ተከትሎ ሳውዲ መራሹ ሐይል በሰንዓ ጥቃት ከፈፀመ በኋላ ነውም መባሉ አይዘነጋም፡፡

የእሳት አደጋውን ተከትሎ ሀውቲ ባወጣው መግለጫ ዓለምአቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅትና የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ለስደተኞቹ መኖሪያ ባለማቅረብና ከየመን እንዲወጡ ለማድረግ ባለመተባበራቸው ለአደጋው ሀላፊነቱን ይወስዳሉ ብሎ ነበር፡፡

አሻርቅ አል-አውሳት ባወጣው ዘገባው በየመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ አደጋ ሀውቲ ተጠያቂ ነው በማለት በዓለም አቀፉ የወንጀሎች ፍርድ ቤት (አይ.ሲ.ሲ) ሊያመሩ መሆኑን አስነብቧል፡፡

ይህን ጉዳይ ይመረዋል የተባለው ተወካይ እንደተናገሩት ፍትሕ ሊረጋገጥ ይገባዋል፤ ለሰሩት ወንጀልም ዋጋቸውን ይከፍላሉ፡፡ስደተኞች ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት ሀውቲን ሲቃወሙ እንደነበረ ዘገባው አስታውሷል፡፡ ባለፈው ሀሙስ ሀውቲ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡትን ሲሰድቡ፣ ሲዘልፉና ሲሞግቱ እንደነበረም ተመላክቷል፡፡

ቀን 23/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply