በየዕለቱ ከ300 በላይ የኮቪድ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ህክምና እንደሚገቡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በየቀኑ ኮ…

በየዕለቱ ከ300 በላይ የኮቪድ ታማሚዎች ወደ ጽኑ ህክምና እንደሚገቡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በየቀኑ ኮቪድ-19 ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው መሆናቸውን እና ከእነዚህ ውስጥ እስከ 50 የሚደርሱት የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ይህን ተከትሎም ለስድስት ወራት የሚቆይ ኮቪድ 19ን የመከላከል ንቅናቄ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በኮቪድ የሚሞቱና ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በየቀኑ ቫይረሱ ከሚገኝባቸው ሰዎች ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑት ጽኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፤ ከዚህ ውስጥ ከ40 እስከ 50 የሚሆኑት ደግሞ የመተንፈሻ አካልን የሚረዳ ማሽን ያስፈልጋቸዋል፡፡ በየቀኑ የሚገለጸው ቁጥር ምርመራ ከተደረገላቸው ውስጥ ብቻ ስለሆነ ትክክለኛውን ቁጥር አያሳይም ያሉት ዶክተር ደረጀ፤ አሁን እየተመረመረ ያለው በቀን ከ4ሺ እስከ 5ሺ ሰው በመሆኑ አሁን ከሚመረመረው በሶስትና አራት እጥፍ ከፍ ቢደረግ ውጤቱም በተመሳሳይ ከፍ ማለቱ እንደማይቀር ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በሽታው የሚገኘው በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እንደነበረና አሁን ላይ ግን ከ900 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች እንደተገኙም ገልጸዋል። ከዚህ በፊት ከተመረመረው ከሶስት እስከ አራት በመቶ ብቻ ቫይረሱ የሚገኝባቸው እንደነበርና አሁን ግን ከ10 እስከ 15 በመቶ በአንዳንድ ቦታዎች ላይም ከ30 እስከ 40 በመቶ ቫይረሱ እየተገኘ መሆኑንም ተናግረዋል። EPA እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply