በዩናይትድ ስቴትስ ቬቴራንስ ዴይ/የአርበኞች ቀን/ እየተከበረ ነው

https://gdb.voanews.com/596e96c5-59a3-414b-aef1-cc7a681ef20a_w800_h450.jpg

በዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይሎች ያገለገሉ አርበኞች የሚከበሩበት እና የሚታሰቡበት ቬቴራንስ ዴይ በሀገሪቱ ዙሪያ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች እና ሠልፎች በዛሬው ዕለት እየተከበረ ነው።

ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሐሪስ የውጭ ሀገር ጉብኝት ላይ ያሉትን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን በመወከል ከመዲናዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ ቨርጂኒያ ውስጥ በሚገኘው በአርሊንግተን ብሔራዊ የአርበኞች መካነ መቃብር  በተከናወነው ሥነ ሥርዓት  የተገኙ ሲሆን ባልታወቀው ወታደር መታሰቢያ ሀውልት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply