
በርካታ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ጥገኝነት ጠያቂ ነፍሰ ጡሮች ለሚለወደው ልጅ የውሸት አባት በመግዛት ቪዛ ለማግኘት እንደሚሞክሩ በቢቢሲ ኒውስናይት የተሠራ የምርመራ ዘገባ አጋለጠ። ድርጊቱ በምን ያህል ጥገኛ ጠያቂዎች የተፈጸመ እንደሆነ ለጊዜው መረጃ ባይኖርም፣ በርካታ ሴቶች በዚህ ዘዴ በዩኬ የመቆያ ቪዛ እንዳገኙ አመላካች ነው ተብሏል። ነፍሰ ጡር እናቶች ለዚህ የውሸት አባት በአማካይ እስከ 10 ሺህ የዩናይትድ ኪንግደም ፓውንድ እንደሚከፍሉ ቢቢሲ ማረጋገጥ ችሏል።
Source: Link to the Post