በ”ያ ቴሌቪዥን” በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ከ10 እስከ 15 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ተባለ፡፡

በ”ያ ቴሌቪዥን”በደረሰ የእሳት አደጋ ከውጪ የገቡ ዘመናዊ የሚዲያ ቁሶች ከ10 እስከ 15ሚሊዮን የሚገመት ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙን ጣቢያዉ በሰጠዉ መግለጫ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አራት በቀድሞው አጎና ሲኒማ ህንጻ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ በፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

በቀጣይ ጣቢያዉ በ ቁጥር አንድ ስቱዲዮ ስራዉን እንደሚቀጥልና ከ12 በላይ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች አሰናድቶ ለተመልካች ለማቅረብ ዝግጅት እያደረገ ነዉ ተብሏል፡፡

ያ ቴሌቪዢን ጣቢያ ከተቋቋመ ሁለት አመት ያስቆጠረ ሲሆን የሩቅ ምስራቅ ፊልሞችን በአማርኛ ትርጉም ለተመልካቾች ሲያቀርብ ነበር፡፡

በስሩም ከ70 በላይ ሰራተኞች ቀጥሮ እያሰራ የሚገኝ ጣቢያ መሆኑንም ሰምተናል።

በልዉል ወልዴ

የካቲት 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply