You are currently viewing በይልማና ዴንሳ ወረዳ የክልልት ቀበሌ አርሶ አደሮች በማደበሪያ አቅርቦት ችግር ክፉኛ መፈተናቸውን ገለጹ፤ የመጣ ማዳበሪያ ቢኖርም የባለ ሀብት ችግኝ ካልገዛችሁ በሚል ከልክለውናል ሲሉ አማረዋ…

በይልማና ዴንሳ ወረዳ የክልልት ቀበሌ አርሶ አደሮች በማደበሪያ አቅርቦት ችግር ክፉኛ መፈተናቸውን ገለጹ፤ የመጣ ማዳበሪያ ቢኖርም የባለ ሀብት ችግኝ ካልገዛችሁ በሚል ከልክለውናል ሲሉ አማረዋ…

በይልማና ዴንሳ ወረዳ የክልልት ቀበሌ አርሶ አደሮች በማደበሪያ አቅርቦት ችግር ክፉኛ መፈተናቸውን ገለጹ፤ የመጣ ማዳበሪያ ቢኖርም የባለ ሀብት ችግኝ ካልገዛችሁ በሚል ከልክለውናል ሲሉ አማረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 17/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምዕራብ ጎጃም ይልማና ዴንሳ ወረዳ የክልልት ቀበሌ አርሶ አደሮች በማደበሪያ አቅርቦት ችግር ክፉኛ መፈተናቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በተደጋጋሚ ተናግረዋል። በተለይ ደግሞ በምግባረ ብልሹ አመራሮች ለነጋዴዎች እየተሸጠ በመሆኑ እጥረቱ ሆንተብሎ እንዲከሰት ተደርጓል ይላሉ። ሀምሌ 17/2015 ደግሞ አዲስ የመጣ ማዳበሪያ አለ ተብለን ወደ ክልልት ቀበሌ ብናቀናም በጣም የተቸገርን መሆናችን እየታወቀ የባለ ሀብት ችግኝ ካልገዛችሁ አንሰጥም በሚል አባረውናል ሲሉ አማረዋል። የአማራ አርሶ አደር በከፍተኛ ሁኔታ የማዳበሪያ አቅርቦት ችግር እያጋጠመው መሆኑን በመግለጽ በልዩ ልዩ መልኩ ተቃውሞ እያቀረበ ቢሆንም እስካሁን ተገቢ የሚባል ምላሽ አለማግቱ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply