በደምቢ ዶሎ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ ኹለት ጭንቅላት ያለው ህፃን መወለዱ ተሰማ

አርብ ነሐሴ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ማስተማሪያ ሆስፒታል ከወትሮው በተለየ መልኩ ኹለት ጭንቅላት ያለው ህፃን መወለዱ ተገለጸ።

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ በሰጡት ማብራሪያ፤ ህፃኑ በኹለት ጭንቅላት መወለዱን በመግለጽ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው እንደሆነና ህፃኑ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወለዱን ተናግረዋል።

በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ እና በእናቶች ማህፀን ውስጥ በሚስተናገዱ እንቁላሎች ብዛት ላይ የተመሰረተ ነው ሲሉ ዶ/ር ፀጋሄዬ አብራርተዋል።

በኢኒስቲትዩቱ የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ አክለውም፤ ክስተቱ በመንታ ምድብ የሚመደብ ሲሆን የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው ብለዋል።

በአኹኑ ጊዜ እናትም ሆኑ ሕፃኗ በጥሩ ኹኔታ ላይ እንደሚገኙም መገለጹን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply